1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አንድ ሆነን እንነሳ፤ ነገን እንገንባ» የኢትዮጵያዉያን ቀን በአዉሮጳ 

ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2011

የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃገር ዉስጥ እና በዉጭዉ ዓለም እየተካሄዳ ያለዉ የዲፕሎማስያዊ ግንኙነት መረሃ ግብር  እንዴት እንደሆን በሰጠዉ መግለጫ ዛሬ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/36nSl
Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

ጥቅምት 21፤ ፍራንክፈርት የኢትዮጵያዉያን ቀን ይከበራል

ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ በመግለጫዉ በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ «ግንቡን እናፍርስ፣ ድልድዩን እንገንባ» በሚል መርሕ ኢትዮጵያዉያን  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድን የማግኘት እንድል የነበረበት ዝግጅት እንደተካሄደ ሁሉ በቀጣይ ይኸዉ አይነት ዝግጅት በአዉሮጳ እንደሚደገም ገልፆአል። ጥቅምት 21 በአዉሮጳ ጀርመን ፍራንክፈርት ላይ የሚከበረዉ  የኢትዮጵያ ዉያን ቀን « አንድ ሆነን እንነሳ፤ ነገን እንገንባ» በሚል መሪ ሃሳብ እንደያዘም ዛሬ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠዉ መግለጫ አመልክቶአል። መግለጫዉን የተከታተለዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል። 


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ 
አዜብ ታደሰ 


ሸዋዬ ለገሠ