1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የጀርመን ጥምር መንግሥትና የአፍሪቃ ፖሊሲዉ

ሐሙስ፣ መጋቢት 6 2010

በአዲሱ የጀርመን ጥምር መንግሥት በግሉ የንግድ ዘርፍ ተጨማሪ የልማት እርዳታ በማድረግ ለአፍሪቃ ቀደምቱን ቦታ መስጠት ይፈልጋል። የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኞች በበኩላቸዉ፤ መንግሥት ለአፍሪቃ ያቀደዉ ልማታዊ የትብብር ዉል ባለፈዉም መንግሥት እቅድ ላይ የሰፈረ ነበር ሲሉ እቅዶቹ ባዶ ተስፋ ሆነዉ እንዳይበኑ ከወዲሁ ያስጠነቅቃሉ።

https://p.dw.com/p/2uPEa
Deutschland G20 Afrika Treffen
ምስል picture-alliance/dpa/K. Nietfeld

አዲሱ የጀርመን የአፍሪቃ ፖሊሲ

በአዲስ በተመሰረተዉ የጀርመን ጥምር መንግስት ዉል መሰረት አህጉር አፍሪቃ 28 ጊዜ በመጠቀስዋ አፍሪቃ አዲስ ለተመሰረተዉ የጀርመን መንግሥት ዋንኛ አጋር አይደለችም ማለት አይቻልም። ምንም እንኳ በጀርመን ፖለቲካ የአካባዉ ጉዳይ ጥላ አጥልቶበት ቢቆይም። በጀርመን ፍራይቡርግ ከተማ የአፍሪቃ ጉዳዮችን የሚያጠናዉ አርኖልድ በርግ ስትራሰር ተቋም የአፍሪቃ ጉዳይ ተመራማሪ አንድርያስ ሜለር እንደሚሉት  ከከዚቀደሙ ጋር ሲነጻፀር በአዲሱ ጥምር መንግሥት ምናልባትም የአፍሪቃ ጉዳይ በስፋት እና ተደጋጋሚ ተነስቶአል።

«እንደ እኔ እምነት በሚደንቅ ሁኔታ አፍሪቃ እየተሰጣትን በጣም ቀዳሚ ቦታ እያጣጣመች ነዉ ማለት እችላለሁ። በዚህ የጥምር መንግሥት ስምምነት ዉል አፍሪቃ በተለያዩ ቦታዎች ጎልታ ትታያለች። ከተሰናባቹ ጥምር መንግሥት ይልቅ በአሁን በአዲሱ የጥምምር መንግሥት ስምምነት ዉል ላይ ይበልጥ ስለአፍሪቃ ጎልቶ ተፅፎ ይታያል ማለት እችላለሁ»

Deutschland Unterzeichnung Koalitionsvertrag
ምስል picture-alliance/dpa/AA/E. Basay

የጀርመን በአፍሪቃ ላይ ጠንከር ያለ ቱክረት መታየቱ በተለይ ጀርመን  የቡድን 20 ሊቀመንበር ከሆነች በኋላ የቀጠለ ነዉ። ባለፈዉ ዓመት ጀርመን የ « ቡድን 20» ሊቀመንበር በሆነችበት ጊዜ ከጎረቤት አህጉር ጋር አዲስ የትብብር ግንኙነትን ለመፍጠር  "ከአፍሪቃ ጋር እኩል" እንዲሁም  "ማርሻል ፕላን ከአፍሪቃ ጋር  የተሰኘ ሁለት መረሐግብሮችን ቀርፃ አርባለች። ይሁን እንጂ  ይህን መረሐ-ግብር ተከትሎ ተግባራዊ የሆነዉ የትብብር ሥራ እስካሁን ግን ጥቂት መሆኑ ተመልክቶአል ። ቢሆንም ይላሉ ለጀርመናዊዉ የክርስትያን ዲሞክራት ፓርቲ አባል የአፍሪቃ ፖለቲካ ጉዳይ ምሁር ፍራንክ ሃይንሪሽ «አፍሪቃን ያካተተዉ 179 ገፆች ያሉት የጀርመን መንግሥት አዲሱ የስምምነት ዉል ጀርመን ጉዳዩን ከልብ እንዳጤነችበት ማሳያ ነዉ» በአዲሱ ጥምር መንግሥት ስምምነት ዉል ላይ አፍሪቃ በተደጋጋሚ በነሳትዋ። የአፍሪቃ ጉዳይ ይተዋል የሚል ሥጋት የለብኝም ሲሉ ፋራንክ ሃይኒርሽ አክለዋል። በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በጀርመን መንግሥት በአፍሪቃ ይተገበራሉ ተብለዉ ዋንና የተብለዉ የተቀመጡት ነጥቦች  ቀጣይነት ይኖራቸዋል።   አዲስ የልማት መዋለ-ንዋይ ፍሰት ሕግ አማካኝነት ብዙ የአነስተኛና ጥቃቅን የንግድ ስራዎች ወደ አፍሪቃ እንዲመጡ ይደረጋል።  የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልየጀርመን ኩባንያዎች ለአደጋ እንዳይጋለጡ በጀርመኑ የዉጭ የብድር እና ዋስትዎች አማካኝነት እንዲሻሻሉ ይደረጋል። የልማት እርዳታዉም መሻሻል ይኖርበታል።  ከሃገራችን የልማት ፖሊሲ የኢኮኖሚ ልማት እንዴት እንደሚጀመር ማወቅ  አለብን፤ ሲሉ ቃል  መግባታቸዉ ይታወሳል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ የኩባንያ ማኅበራት ጥምረት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እስካሁን አመርቂ ስኬትን አላገኙም። የአፍሪቃ የጀርመን ንግድ ማህበር ሊቀ መንበር ስቴፈን ሊቤሊንግ  በበኩላቸዉ « ያለፉት ጊዜያት የፈፃፀሞች ጉድለቶች ይስተካከሉ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ሊቤሊንግ በአዲሱ የአፍሪቃ ፖሊሲ መረሐ ግብር  በተቻለ ፍጥነት አሁን ተጨባጭ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። ባለፉት ጊዜያት የታቀዱ ስራዎች እዉን ባለመሆናቸዉ መንግስት በአፍሪቃ የግል ዘርፉን መዝጋት በመፈለጉ፤ በርካታ ኩባንያዎች ጥንቃቄ መዉሰድ እንዲጀምሩ አድርጓዋል። «ብዙዎቹ ያረጁ ዉሎች» በመሆናቸዉ የጀርመን ኩባንያዎች በብዛት ይሄዳሉ ብለን መጠበቅ የለብንም ሲሉ የአፍሪቃ ጉዳይ ተመራማሪዉ አንድርያስ ሜለር ተናግረዋል። ምጡቅ የሆኑ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ወደ አፍሪቃ ገበያ መዉሰድ የሚፈልጉት የጀርመን ኩባንያዎች በአፍሪቃ የገበያ መድረክ በአብዛኛዉ ተፈላጊ አለመሆናቸዉን ሜለር አስምረዉበታል።  የጀርመን መንግሥት የሚሰጠዉን ልማት ዕርዳታ መጨመር ቢፈልግም በአፍሪቃ የሲቪል ማህበረሰቡ እና ተቃዋሚዎች ነገሩን በተመለከተ ያላቸዉ አስተያየት በጥንቃቄ የተሞሉ ናቸዉ። ምክንያቱ ወደፊት የመከላከያ ወጪዎች መጨመር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነዉ። ለሁለቱ ዘርፎች ማለት ለልማት ርዳታና ለመከላከያ የሚሆን ወጭ በድምሩ ወደ ሁለት ቢሊዮን ዩሮ ተመድቦአል። በጀርመን የአረንጓዴዉ ፓርቲ የልማት መምርያ ቃል አቀባይ ኡቨ ኬክሪትዝ ፤ ለልማት ርዳታ እንደሚሰጠዉ ዉ ሁሉ ለመከላከያ ድጋፉም ያን ያህል ወጭዉ ይጨምራል የሚል እምነት እንደሌላቸዉ ገልፀዋል።

Südafrika Volkswagen in Johannesburg
ምስል picture-alliance/dpa/F. Gentsch

«አንድ እኩል የሆነ ማለትም ለመከላከያ ከሚሰጠዉ ድጋፍ ለለማት ርዳታዉ ከሚሰጠዉ ድጋፍ በፍጥነት ያድጋል የሚል እምነት የለኝም »    

ለአፍሪቃ ሌሎች ቃል የተገቡ ነገሮች ሁሉ ተፈፃሚነት ያግኙ አያግኙ እስካሁን ምንም ግልፅ የሆነ ነገር የለም። በሚቀጥሉት ዓመታት ጀምሮ የጀርመን ውጭ ፖሊሲ ትኩረት በምዕራብ አፍሪቃ ይሆናል። በሳህል አካባቢ ሃገራት ጀርመን ለበርካታ ዓመታት አክራሪ እስልምና ተከታዮች እና የተደራጁ ወንጀለኞችን ለመዋጋት የምታደርገዉን ድጋፍ አጠናክራ መቀጠል ትፈልጋለች። በነዚህ ሃገራት አካባቢ ወደ አዉሮጳ የሚሻገሩ ስደተኞች የሚጓጓዙበት ዋንና መስመር መሆኑም እሙን ነዉ።  በሌላ በኩል የጀርመን የአፍሪቃ ፖሊሲ ላይ ያልተጠቀሰ ዋና ጉዳይ ቢኖር አዲሱ የጀርመን ጥምር መንግሥት በአፍሪቃ በነበረዉ የቅኝ ግዛት ዘመን ያሳደረዉን ተፅኖ ከሃገራቱ አጋር ባልደረቦች ጋር ለመፍታት እንደሚፈልግ ዉሉ ላይ መስፈሩ ነዉ። ይሁን እንጂ  በደቡብ ምስራቅ አፍሪቃ ላይ በምትገኘዉ በቀድሞዋ የጀርመን ቅኝ ግዛት ሃገር በዛሬዋ ናሚቢያ የዘመናት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበትን የሚያሳይ ግልጽ የሆነ መረጃ የለም።  የሁለቱም ሃገራት መንግሥታት ከጎርጎረሳዊ  2015 ጀምሮ በጉዳዩ ላይ ቢመክሩም ያገኙት ዉጤት የለም። በሁለቱ ሃገራት መካከል የተካሄደዉ መቋጫ ያጣዉ ድርድር በናሚቢያ ተስፋ መቁረጥና  እና ንዴትን ቀስቅሶአል። አዲሱ የጀርመን ፌዴራል መንግሥት ድርድሩን በተሳካ ሁኔታ ካላጠናቀቀ በአካባቢዉ ላይ ቢያንስ ተቀባይነቱን  ሊያጠለሽ ይችላል።

Bundesentwicklungsminister Müller in Äthiopien
ምስል picture-alliance/dpa/K. Nietfeld

አዜብ ታደሰ /  ዳንኤል ፔልዝ  

ሸዋዬ ለገሠ