1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አፍሪካሜራ» በርሊን 2018  

ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2011

ዘንድሮ በተለይ በአፍሪቃዉ ቀንድ የሚገኙ ሃገራት የፊልም ሥራዎቻቸዉን ይዘዉ በርሊን መድረክ ላይ ታድመዋል። ከነዚህ መካከል ኢትዮጵያዉያኑ የፊልም ሥራ ባለሞያዎች ይገኙበታል። ይህ የፊልም ሥራ ባህል ልዉዉጥን ከማዳበሩም በላይ የምዕራቡ ዓለም በአፍሪቃዉ ቀንድ ስላለዉ አመለካከት ያስቀይራል የሚል ግምት ተሰጥቶታል።

https://p.dw.com/p/38J2N
Logo AFRIKAMERA 2018
ምስል DW/Y. Hinz

«አፍሪቃዉያን አዳዲስ ፊልሞች በበርሊኑ መድረክ»

«አፍሪካሜራ» አዳዲስ ፊልሞች ከአፍሪቃ በሚል ርዕስ በየዓመቱ በጀርመን መዲና በርሊን ላይ አፍሪቃዉያን ወጣት የፊልም ሥራ አዋቂዎች ፊልሞቻቸዉን ለመዲናይቱ ነዋሪዎች እና የፊልም ሥራ ባለሞያዎች ለእይታ ያቀርባሉ።  ዘንድሮ በተለይ በአፍሪቃዉ ቀንድ የሚገኙ ሃገራት የፊልም ሥራዎቻቸዉን ይዘዉ በርሊን መድረክ ላይ ታድመዋል። ከነዚህ መካከል ኢትዮጵያዉያኑ የፊልም ሥራ ባለሞያዎች ይገኙበታል። የብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ መስራች አብረሃም ኃይሌ ብሩ አንዱ ናቸዉ።አፍሪቃዉ ቀንድ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ በተለይ የሚታወቀዉ አካባቢዉ ላይ ባሉ ሃገሮች ዉስጥ በሚታየዉ የርስ በርስ ግጭትና በስደት ነዉ። በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ኅዳር አራት እስከ ፊታችን እሁድ ኅዳር አስር በጀርመን በርሊን መዲና ላይ እየተካሄደ ባለዉ የፊልም መድረክ በተለይ ከምስራቅ አፍሪቃ በተለይም ደግሞ ከአፍሪቃዉ ቀንድ አካባቢ ሃገራት የፊልም ሥራ ባለሞያዎች በሃገሮቻቸዉ  ለእይታ ያበቅዋቸዉን አዳዲስ ፊልሞችን ይዘዉ በበርሊኑ የፊልም መድረክ ላይ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።  ተሞክሮቻቸዉንና በየሃገሮቻቸዉ ለፊልም ሥራ ተግዳሮት ያሉዋቸዉን ነጥቦችን እያነሱም ይወያያሉ። ይህ የፊልም ሥራ ባህል ልዉዉጥን ከማዳበሩም በላይ የምዕራቡ ዓለም በአፍሪቃዉ ቀንድ ስላለዉ አመለካከት ያስቀይራል የሚል ግምት ተሰጥቶታል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከኢትዮጵያ ወደ ጀርመን መዲና በርሊን ፊልሞቻቸዉን ይዘዉ የመጡ የፊልም ሥራ ባለሞያ ኢትዮጵያዉያንን አነጋግሮ ሰፋ ያለ ዝግጅቱን ልኮልናል። ሙሉዉን መሰናዶ ለማድመጥ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 

አብረሃም ኃይሌ ብሩ
ምስል DW/Y. Hinz


ይልማ ኃይለሚካኤል 


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ