1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የወደብ ፍለጋ

እሑድ፣ ግንቦት 5 2010

ለበርካታ ዓመታት በአመዛኙ የጅቡቲ ወደብ ተጠቃሚ ሆና የቆየችው ኢትዮጵያ የባለቤትነት ድርሻ የሚያሰጡ የወደብ ልማቶችን በጎረቤት ሀገራት ለማካሄድ ወደ ሚያስችል ደረጃ መሸጋገርዋ እያነጋገረ ነው።

https://p.dw.com/p/2xYzn
Dschibuti Containerhafen und Rotes Meer
ምስል Getty Images/AFP/S. Maina

ኢትዮጵያ እና አነጋጋሪው የወደብ ፍለጋዋ

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ነጻ መንግሥት ከመሠረተች ወዲህ ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ በአመዛኙ የጅቡቲ ወደብ ተጠቃሚ ናት። ኢትዮጵያ ከ90 በመቶ በላይ የወጪ ንግዷን የምታስተናግደው በጂቡቲ ወደቦች በኩል ነው።  ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ የጅቡቲን ጨምሮ የሌሎች ጎረቤት አገራት ወደቦችን ከከዚህ ቀደሙ በተለየ መንገድ  መጠቀም የሚያስችላት ጥረቶችን ጎን ለጎን እያካሄደች ነው። ከወራት በፊት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እውቅና ያልተሰጣትን የሶማሌላንድን የበርበራ ወደብ በማልማት የባለቤትነት ባለድርሻ የሚያደርጋት አነጋጋሪ ስምምነት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ተፈራርማለች። በሰሞኑ የአዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የጎረቤት አገራት ጉብኝት ወቅትም የወደብ ጉዳይ ትኩረት ከተሰጣቸው ውስጥ አንዱ ነበር። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በጎበኙዋቸው በጅቡቲ በሱዳን እና በኬንያ ኢትዮጵያ በሀገራቱ ወደቦችን አብሮ ለማልማት የሚያስችሉ መግባባት እና ስምምነቶች ላይ መድረሷ ተነግሯል። ለበርካታ ዓመታት በአመዛኙ የጅቡቲ ወደብ ተጠቃሚ ሆና የቆየችው ኢትዮጵያ  የባለቤትነት ድርሻ የሚያሰጡ የወደብ ልማቶችን በጎረቤት ሀገራት ለማካሄድ ወደ ሚያስችል ደረጃ ማምራቷ ወይም መሸጋገርዋ እያነጋገረ ነው። ኢትዮጵያ እና አነጋጋሪው የወደብ ፍለጋዋ የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩት ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ በአሜሪካን ኢሊኖይስ ዩኒቨርስቲ የኤኮኖሚክስ መምህር ፣ አቶ ጌታቸው ተክለ ማርያም የኢንቬስትመንት አማካሪ እና የኤኮኖሚ ምሁር እንዲሁም አቶ ቻላቸው ታደሰ የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው።

ሙሉውን ውይይት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ