1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወጣቶች በኬንያ

ዓርብ፣ ግንቦት 30 2011

ወጣት ብሩን ጨምሮ አዳፋ ልብስ የለበሱና የፕላስቲክ ከረጢት ፌሽታል ያንጠለጠሉ ወጣቶች በኬኒያ የጆሞ ኬኒያታ አውሮፕላን ማረፊያ ተኮልኩለው ይታያሉ። የኬኒያ ፖሊስ ተጠርዘው ወደመጡበት ኢትዮጲያ እንዲመለሱ ውሳኔ ያሳለፈባቸው እነኘሁ ወጣቶች ለወራት የረሀብና የጉስቁልና መከራ ያዩበትን ምድር ለቀው ለመውጣት የቀራቸውን የሰዓታት ዕድሜን ይጠባበቃሉ ።

https://p.dw.com/p/3K35x
Karte Sodo Ethiopia ENG

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ከናይሮቢ አየር ማረፊያ እስከ አዲስ አበባ

በኢትዮጲያ በፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምክንያቶች በቡዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ተለያዩ አገራት ይፈልሳል።ከእነኝሁ ፍልሰቶች መካከል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሸጋገር የሚደረገው ጉዞ በቀዳሚነት ይጠቀሳል።ወጣት ብሩ ጋዲሴ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሸጋገር የኬኒያን ግዛት በማቋረጥ ላይ እንዳለ በፖሊሶች እጅ ከወደቁት በርካታ ኢትዮጲያዊያን መካከል አንዱ ነው ። ወጣት ብሩን ጨምሮ አዳፋ ልብስ የለበሱና አነስተኛ የፕላስቲክ ከረጢት ወይም ፌስታል ያንጠለጠሉ ወጣቶች በኬኒያ የጆሞ ኬኒያታ አውሮፕላን ማረፊያ ተኮልኩለው ይታያሉ። የኬኒያ ፖሊስ ተጠርዘው ወደመጡበት ኢትዮጲያ እንዲመለሱ ውሳኔ ያሳለፈባቸው እነኘሁ ወጣቶች ለወራት የረሀብና የጉስቁልና መከራ ያዩበትን ምድር ለቀው ለመውጣት የቀራቸውን የሰዓታት ዕድሜን ይጠባበቃሉ።

ደቡብ አፍሪካ በበርካታ ኢትዮጲያዊያን ወጣቶች ዘንድ የተስፋይቱ ምድር ተደርጋ ተቆጠራለች ። የዚህ አመለካከት ውልደትም ሆነ ዕድገት በወጣቶቹ የተሻለ ኑሮን በማለም ከአገር ለመውጣት ካላቸው የበረታ ፈላጎት ብቻ የመነጨ አይደለም ። በልጅ ያልፍልኛል የሚለው የወላጆች የተሳሳተ እሳቤም ለወጣቶቹ ፍልሰት ያራሱን በጎ ያልሆነ አስተዋድኦ አበርከቱል የሚሉ ብዙዎች ናቸው ። በዚህም የተነሳ የእርሻ በሬያቸውን አሊያም መሬታቸውን ቆርሰው በመሸጥ ልጆቻቸውን ወደአዚችው መከረኛ አገር የሚሰዱ ወላጆች ቁጥርም ቀላል አለመሆኑ ነው የሚነገረው። 
ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመሻገር በሚደረግው ሙከራ ጥቂቶች በለስ ቢቀናቸውም በርካቶች ግን ወይ በመንገድ ሞተው ይቀራሉ አሊያም ተጠርዘው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ። 
በኬኒያው የጆሞ ኪኒያታ አውሮፕላን ማረፊያ በፖሊስ ጥበቃ ስር ሆነው ያገኝሃቸው ኢትዮጲያዊያን ወጣቶች የዚሁ ህገ ወጥ ስደት አሰከፊነት ማሳያ ሊሆኑ ይችላሉ። ከኬኒያ የጥበቃ ፖሊስ አባላት ባገኝሁት ይሁንታ ቀረብ ብዬ ካነጋገርኳቸው ወጣቶች መካከል አብዛኞቹ ከደቡብ ክልል ሃድያና ከንባታ ጠንባሮ ዞን መምጣታቸውን ገልጸውልኛል። 

ብሩ ጋዲሴና ጋደኞቹ ከወራት በፊት በደቡብ ኢትዮጲያ ሞያሌ በኩል ድንበር አቋርጠው ከወጡ በሃላ የየብስ ትራንስፖርት በመጠቀም ኬኒያ መግባታቸውን ይናገራሉ። 
ጉዛቸውን የጀመሩት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዘመዶቻቸው በኬኒያ ከሚገኙ አሸጋጋሪ ደላሎች ጋር በስልክ ባደረጉት ግንኙነት መሆኑን የሚገልፁት ወጣቶቹ አሸጋጋሪ የተባሉትን ግለሰቦች በስምም ሆነ በመልክ እንደማያውቋቸው ይናገራሉ። 
ያም ሆኖ ግን እነኝሁ አሸጋጋሪዎች በሚልኩላቸው ሞተርኞ አማካኝነት የፍተሻ ጣቢያዎችን በማለፍ ናይሮቢ ከተማ መግባታቸው ገልጸውልኛል ። 

ወጣቶቹ እንደሚገልፁት ናይሮቢ ከተማ ከገቡ በሃላ ቀጣይ ጉዞቸውን ለማመቻቸት በአንድ ሰዋራ መንደር ውስጥ ለሁለት ሳምንታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ተደብቀው ቆይተዋል ። 
በመንደሩ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ አስከ ሃምሳ ከሚደረሱ ሰዎች ጋር ተቀላቅለው እንዲያርፉ ከመደረጋቸውም በላይ ምግብና ወሃ በየሁለትና በየሶስት ቀናት ልዩነት ይቀርብላቸው እንደነበር ይናገራሉ። 

Ebola-Ausbruch im Kongo
ምስል Reuters

አነ ብሩ ጋዲሴ ከዚህ ሁሉ በሃላ ቀጣይ ጉዞቸውን ወደ ታንዛኒያ ለመድረግ በዝግጅት ላይ አንዳሉ በኬኒያ የጸጥታ አባላት እጅ በመውደቅ ለቀናት ለእስር ተዳርገዋል። 
በመጨረሻ ግን የኬኒያ ፖሊሶች በህገ ወጥ መንገድ መግባታቸውን በማረጋገጣቸው ኢትዮጲያ ሊመልሶቸው ወደ ጆሞ ኬኒያታ አውሮፕላን ጣቢያ ያመጦቸው ቢሆንም ከእስር ቆይታቸው ጀምሮ ምግብ የሚያቀርብላቸው አካል ባለመኖሩ ለረሀብ መዳረጋቸውን ነግረውኛል። 

Nairobi Skyline Kenia Stadtansicht
ምስል Fotolia/Natalia Pushchina

በኬኒያ ፖሊሶች ወደ ኢትዮጲያ እንዲመለሱ የተደረጉትን ወጣቶችን ያሳፈረው የኢትዮጲያ አየር መንገድ ከሰአታት ጉዞ በሃላ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ሲደርስ በብሩ ጋዲሴና በጋደኞቹ ፊት ላይ የተዘበራረቁ ስሜቶችን አስተውያለሁ። በእርግጥ የጉዞቸው መጨናገፍ ቅር ቢያሰኛቸውም በሰላም ወደ አገራቸው በመመለሳቸው ግን ደስተኛ የሆኑ ይመስላል። 
ቀጣይ ጉዞቸውን በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮ ዞን ወደሚገኘው የትውልድ መንደራቸው ለማቅናት በዝግጅት ላይ እንዳሉ ምንተሰማቸሁ ስል ላነሳሁላችው ጥያቂ በአጭሩ ምላሽ ገልጸውልኛል። 

አቶ ታሪኩ በዛብህ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ ስምሪትና ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው። 
በክልሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረገው ህገ ወጥ ስደት በሃድያና በከንባታ ዞኖች የሚገኙ ወጣቶች የችግሩ ግንባር ቀደም ተጠቂዎች መሆናቸውን አቶ ታሪኩ ይናገራሉ። 
 
የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዞኖቹ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ በህገ ውጥ ስደት ዙሪያ ግንዛቤ የመፈጥር ሰራዎችን በማከናውን ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ ታሪኩ በዚህም አንዳራዊ ለውጦች መታየታቸውን ይገልዳሉ። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ