1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ1 ሺህ በላይ ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኩባንያዎች መታገዳቸው

ሰኞ፣ የካቲት 25 2011

https://p.dw.com/p/3EPgJ
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

ርምጃው ይቀጥላል ተብሏል

የአዲስ አበባ አስተዳደር የሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሕገወጥ አሠሪ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን አገደ። በአዲስ አበባ 1034 ፍቃድ ሳይኖራቸው በስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲነት ሲሰሩ መቆየታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ይፋ አደረገ፡፡ ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው። 

በተለያ ተቋማት የተውጣጣ ግብረ ሃይል ባደረገው የተደራጀ ቁጥጥር አብዛኛው የዘርፉ ስራ ለህገወጥነት ተጋላጭ ሆኖ መቆየቱን ቢሮው አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይ 20 መሰል ተቋማት ሃሰተኛ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ ህዝብ ሲያምታቱና ሲያጭበረብሩ መቆየታቸውን የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ አልምጸሃይ ጳውሎስ ለ DW ተናግረዋል፡፡
ፍቃድ ባወጡበት ቦታ አለመገኘት ፡ አላግባብ ገንዘብ መቀበል፡ ህጋዊውን የፈቃዱን መስፈርት ሳያሟሉ በስራ ላይ መገኘት ኤጀንሲዎቹ የተገኘባቸው ችግር ሲሆን አብዛኞቹም እየታሸጉ ነው ተብሏል፡፡
ለተቀጣሪ ሰራተኞች ስል ክፍያና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ግልጽ የሆነ መረጃ አለመስጠትም ለውዝግብ ምንጭ መሆኑን ቢሮው አደረግኩት ባለው ማጣራት ደርሸበታለሁ ብሏል፡
እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ህዝቡም ህጋዊ የሆኑትን ለይቶ እንዲጠቀም እና በህገወጦች ላይ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተስፋለም ወልደየስ