ከእግር ኳስ እስከ ድምፃዊነት
እሑድ፣ ሐምሌ 29 2010ማስታወቂያ
ባሕላዊዉን ዜማ እና ጭፈራዉን ሲለዉ እንደ ጎጃሞች፤ ሲፈልገዉ እንደ ሸዋዎች፤ ደግሞ እንደ ወሎዎች ያስኬደዋል።እሱ ሁሉንም ሆነ አንዱን፤ ፍላጎት፤ ዝንባሌ ችሎታዉ ባንድ የሚጠቃለል ነዉ።ባሕል።የማንጎራጎር፤መድረስ ስሜቱ የሚነቃቃዉ ደግሞ ከከተማዉ ከበር ቻቻ ገለል ቀለል ወዳለዉ ገጠር ሲሔድ ነዉ።አሸብር በላይ።ግጥም ይፅፋል።ዜማ ይደርሳል።ድምፃዊዉም ነዉ።ወታደር ነበር።እግር ኳስ ተጫዋችም።ብቻ ባሕል ሙዚቃዉ ላይ አሳረገ። ያፍታ እንግዳችን አድርገነዋል።
ነጋሽ መሐመድ