1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ

Pinado Waba
ዓርብ፣ መጋቢት 11 2012

ታሪኩ የሚያጠነጥነው ማጋሪያ በምትባል በአንዲት የአፍሪቃ ትንሽ ከተማ በግብርና በሚተዳደሩ ሰዎች ላይ ነው። ይቺ ከተማ በተደጋጋሚ በጎርፍ እና በኮሌራ ወረርሽኝ ስትጠቃ ቆይታለች።

https://p.dw.com/p/4Yb9Y
DW Crime Fighters Serienmotiv „Uneasy choices“

ይቺ ከተማ በተደጋጋሚ በጎርፍ እና በኮሌራ ወረርሽኝ ስትጠቃ ቆይታለች። በተለይ ደግሞ ገበሬዎች ተክል ተክለው የጎመራ አዝመራቸውን ለመሰብሰብ በሚፈልጉበት ዝናባማ ወቅት! ታዲያ ካለፉት ዓመታት አንስቶ የአየር ንብረቱ እጅጉን በመለወጡ ነገሮች ሁሉ ተባብሶባቸዋል። ለረዥም ዓመታትም ማኅበረሰቡ ለችግሩ ምንም መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም ነበር። በዚህ ዓመት ግን የሕዝቡን ሕይወት ለማሻሻል የገንዘብ ድጋፍ ተገኝቷል። ይህ ደግሞ እንደ ሃይማኖት እና ጓደኞቿ ካሪማ  እንዲሁም ሲሳይ ላሉ የማኅበረሰቡ ወጣቶች አስደሳች ዜና ሆኗል። ሦስቱ ወጣቶች የዩንቨርስቲ ትምህርታቸውን ለአንድ ዓመት አቋርጠው በቅርቡ በተመመሰረተው የአባባቢ እና ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት በነፃ ሲያገለግሉ ሃይማኖት የማጋሪያ ከተማ ከንቲባን መጠራጠር ትጀምራለች።  በእርግጥ ገንዘቡን ለህብረተሰቡ ጥቅም ማዋል ይፈልጋሉ? ወይስ ሌላ ነገር አለ?  ለሶስቱ ጓደኛሞች የበጎ ፈቃደኝነት አመታቸው በፍጥነት ወደ ቅዠት ይቀየራል። 

 

 

ደራሲ: ፒናዶ አዳማ ዋባ

ትርጉም: ልደት አበበ

ዝግጅት: ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ