1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላስ ቬጋሱ ግድያ ምርመራ ከምን ደረሰ?

ሐሙስ፣ መስከረም 25 2010

ነርስ ልትሆን የወጠነች የ20 አመት ኮረዳ በወንድ ጓደኛዋ ክንድ ላይ ለዘላለም አሸለበች። አራስ ልጇን ከቤት ትታ ዘና ለማለት የወጣችው እና በወሊድ ፈቃድ ላይ የነበረችው የአራት ልጆች እናት እንዳቀደችው አልተመለሰችም።

https://p.dw.com/p/2lIcN
Las Vegas trauert nach dem größten Massenschießen in der U.S. Geschichte
ምስል picture-alliance/N.Otto

የላስ ቬጋስ ጥቃትና ምርመራው

 ከማኅበረሰባዊው የሙዚቃ ድግስ ትዳር የመረተበትን ጊዜ ቆጥሮ በደስታ ሊያከበር የወጣው ባል ድንገት ከ32ኛ ፎቅ ከሚዘንበው የጥይት እሩምታ ባለቤቱን ታድጎ ሞተ። ሥመ-ጥሩ የሚባሉት የአሜሪካ የሥለላ ተቋማት ዛሬም ድረስ  ስቴፈን ፓዶክ በላስ ቬጋስ ከተማ 58 ሰዎች ለመግደል ስላነሳሳው ምክንያት በቂ መረጃ የላቸውም። በእርግጥ ባለሥልጣናቱ ፓዶክ ቁማር ወዳድ ጡረተኛ እንደነበር አልጠፋቸውም። የመኖሪያ ቤቱን ጨምሮ በስሙ የተመዘገቡ 47 የጦር መሳሪያዎችንም አግኝተዋል። ለመሆኑ ምርመራው ከምን ደርሶ ይሆን?


መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ