1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕሙማን መጠለያ ተገነባ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2011

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተለይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ታካሚዎችን የመጠለያ ችግር ለመቀነስ ታቅዶ የተገነባ ሕንፃ ተመረቀ።

https://p.dw.com/p/3GzOL
Äthiopien Deutsche Botschaft Fun for food
ምስል DW/G. Hailegiorgis

«ከ100 በላይ ሕሙማን ከነአስታማሚዎቻቸው ያስተናግዳል»

 

ሕንፃው ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሟላት በኩልም የጀርመን ኤምባሲ ልዩ በጀት ሲመድብ የኤምባሲው ባልደረቦች ደግሞ መዋጮ በማደረግ መተባበራቸውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። መጨለያው የተገነባው በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እና በቃሊቲ የግንባታ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ ትብብር መሆኑም ተገልጿል። የታካሚዎቹ ማረፊያ 52 ሕሙማን ከነአስታማሚዎቹ በጠቅላላ 104 ሰው የማስተናገድ አቅም አለው።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ