1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸዉ ተገናኙ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2013

ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከየቤተሰቦቻቸዉ ጋር እንዲቀየጡ የተባበሩት መንግስታት ይረዳቸዉ ዘንድ የተማሪዎቹ ወላጆችና ቤተሰቦች ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ዉስጥ ባደረጉት ሰልፍ ጠይቀዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/3y8wC
Äthiopien | Demonstration von Eltern in Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

     

መቀሌ-ትግራይ ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ከ700 በላይ ተማሪዎች አፋር ክልል በሚገኘዉ በሰመራ-ዩኒቨርስቲ በኩል ቤተ-ሰቦቻቸዉ ወደየሚገኙበት አካባቢ መጓዛቸዉ ተነገረ። ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከየቤተሰቦቻቸዉ ጋር እንዲቀየጡ የተባበሩት መንግስታት ይረዳቸዉ ዘንድ የተማሪዎቹ ወላጆችና ቤተሰቦች ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ዉስጥ ባደረጉት ሰልፍ ጠይቀዉ ነበር። የአፋር ክልልላዊ መንግስት ለዶቼ ቬለ እንደገለፀዉ በሁለት ዙር ጉዞ ሠመራ የገቡት ተማሪዎች 725 ናቸዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ያነጋገራቸዉ የተማሪዎቹ ወላጆች እንዳሉት ደግሞ ተማሪዎቹ ሠመራ የገቡት ከብዙ ችግር በኋላ ነዉ።
ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ