1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጨረሻው ሽኝት በአዲስ አበባ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 18 2011

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ላይ በመኖሪያ ቤታቸው በገዛ ጠባቂያቸው ወይም አንጋቻቸው መገደላቸው የተነገረው ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በጡረታ ላይ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ አስከሬን ዛሬ በክብር ተሸኘ።

https://p.dw.com/p/3L4bf
Screenshot Facebook Livestream Trauerfeier Äthiopien Armeechef
ምስል Facebook/etv

በሚሊኒየሙ አዳራሽ የተካሄደው ሥርዓት

በመጨረሻው የክብር ስንብት ላይ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። በስነሥርዓቱ ወቅትም የሁለቱም የጦር ጀነራሎች የሕይወት ታሪክ የተነበበ ሲሆን፤ በቅርበት የሚያውቋቸው ባልደረቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው ታሪካቸውን ለታደሙት በማካፈል በህልፈታቸው ቁጭት ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ልጆቻቸውን እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችም የየበኩላቸውን መልእክት አስተላልፈዋል። በስፍራው ተገኝቶ የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ያጠናቀረውን ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ