1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣኑን ያስረክብ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2011

የአፍሪቃ ኅብረት የሠላምና የፀጥታዉ ኮሚሽን በሱዳን ስልጣን ይዞ የሚገኘዉ ወታደራዊ ኃይል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሥልጣኑን እንዲያስክብም ትዕዛዝ አስተላለፈ። ሱዳንን ለ30 ዓመታት የገዙትን ፕሬዝደንት ኦማር አል በሽርን ከሥልጣን ያሰናበተው የሀገሪቱ የጦር ኃይል በሲቪል አስተዳደር እንዲተካ የሚጠይቁት ተዋቃሚዎች እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው።

https://p.dw.com/p/3Gnxg
Äthiopien AU in Addis Abeba
ምስል DW/G. Giorgis

የአፍሪቃ ኅብረት የሠላምና የፀጥታዉ ኮሚሽን በሱዳን ስልጣን ይዞ የሚገኘዉ ወታደራዊ ኃይል በሃገሪቱ የሽግግር መንግሥት ምስረታን በሚመለከት ዉይይት አካሄደ። የአፍሪቃ ኅብረት ፕሬዚዳንት ሙሳፋኪ መግለጫ በሰጡ ከቀናት በኋላ ሙሉቀን ያስቆጠረ ዝግ ስብሰባ ካካሄደ በኋላ የአቋም መግለጫዉን አዉጥቶአል። የፀጥታዉ ኮሚሽን እንደገለፀዉ « በሱዳን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ስልጣን ይዤ እቆያለሁ ያለዉን ወታደራዊ መንግሥት አዉግዞአል፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሥልጣኑን እንዲያስክብም ትዕዛዝ አስተላልፎአል። ሱዳንን ለ30 ዓመታት የገዙትን ፕሬዝደንት ኦማር አል በሽርን ከሥልጣን ያሰናበተው የሀገሪቱ የጦር ኃይል በሲቪል አስተዳደር እንዲተካ የሚጠይቁት ተዋቃሚዎች እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ