1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ አጋሮች ጉባኤ በብራስልስ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2010

ለሁለት ቀናት ብራስልስ ቤልጅ ላይ የተካሄደው የሶማሊያ አጋሮች ጉባኤ ዛሬ በስኬት መጠናቀቁ እየተነገረ ነው። ስብሰባው የተጠራው እና የተስተናገደው፤ በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት፣ በአውሮጳ ሕብረት እና በስዊድን መንግሥት በጋራ ነው።

https://p.dw.com/p/31hc1
Somalia Partnership Forum in Brussels
ምስል picture-alliance/AA/D. Aydemir

ስብሰባው በስኬት መጠናቀቁ ተነግሯል፤

 

 

በጉባኤው ላይም ከሶማሊያ ከመጡ የመንግሥት እና ሲቪክ ማሕበራት ተወካዮች በተጨማሪ የ58 ሃገራት እና የስድስት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ልዑካንም ታድመዋል። ስብሰባው ሲጠናቀቅም ሶማሊያ መንግሥት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ለጋሾች በሶማሊያ የተረጋጋ የፖለቲካ እና ኤኮኖሚያዊ ሥርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማረጋገጥ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። ከብራስልስ ገበያው ንጉሤ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

Somalia Partnership Forum in Brussels
ምስል picture-alliance/AA/D. Aydemir

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ