1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀይ ባሕር ዓፋር ዴሞክራስያዊ ድርጅት

ዓርብ፣ የካቲት 1 2016

እንደ አቶ ያሲን፣ በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ ብዙ ግፍ እየደረሰበት እና እየተሰደደ ያለው ወጣቱ ክፍል ነው። «በአብዛኛው ወጣቱ ተሰዳጅ ነው። አሁን ብዙ ግፍ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ ዋናው ተጠቂው አብዛኛው የቀይ ባሕር አፋር ወይም የኤርትራ ሕዝብ ወጣቱ ነው አብዛኛው። ይህ ክፍል ደግሞ ዛሬ በስደት ላይ ይገኛል።»

https://p.dw.com/p/4cE78
የኤርትራ ወደብ ከተማ ሂርጊጎ
የኤርትራ ወደብ ከተማ ሂርጊጎ ምስል PETER MARTELL/AFP/Getty Images

በውጪ የሚኖሩ የቀይ ባሕር አፋር ወጣቶች ጥሪ

በውጪ የሚኖሩ የቀይ ባሕር አፋር ወጣቶች ጥሪ


የቀይ ባህር አፋር ዲያስፖራ ወጣቶችና ሌሎች ተወካዮች፣ በኦሃዩ ክፍለ ግዛት ኮሎምበስ ከተማ ሰሞኑን ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደዋል። ከስብሰባው አስተባባሪዎች መኻከል ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው ፣በሰሜን አሜሪካ የቀይ ባሕር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅትና ወጣቶች ተወካይ አቶ አብዱ አሚን፣ጉባዔው የተካሄደበትን አላማ  በተመለከተ እንደሚከተለው ገልፀዋል።

«ዋናው ዓላማ፣ አምባገነኑ የሻዕቢያ መንግሥት በቀይ ባህር አፋር ህዝብ ላይ የሚፈጽመው ግፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፋፋመ ስለሆነ የቀይ ባሕር አፋር ህዝብ በስደት እና የቀሩትም በእስር እየተንገላቱ ስለሆነ፣ ይህንን አፈናና ዲሞክራሲያዊ ያልሆነ ሰብዓዊ ረገጣ የሚፈጽመውን  ስርዓት ለመደምሰስ ወጣቶቹ በአንድ ላይ ተነስተው  የቀይ ባሕር አፋር ወጣቶች ስብሰባውን አካሄደዋል።

የጉባዔው የአቋም መግለጫ

ተሰብሳቢዎቹ ባካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ የቀይ ባሕር(የዳንካሊያ) አፋር ሕዝብ ላለፉት ዓመታት አምባገነን ባሉት የኤርትራ መንግሥት ለከፍተኛ ግፍና ጭቆና መዳረጉን አስታውቀዋል።  በቀይ ባሕር አፋር ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና እና ጭቆና እየተባባሰ ሄዶ፣ ወደ ብሔር ተኮር ጭቆና እና አፈና ተሸጋግሮ ይገኛልም ብለዋል።

 ከዚህ ነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት፣ የቀይ ባሕር ዓፋር ህዝብ ከዚህ አስከፊ ጭቆና እና ብሔር ተኮር አፈና ነጻ ወጥቶ፣ ሰላምና ደህንነቱን እንዲያረጋገጥ የሚያደርገው ትግልና እንቅስቃሴ በተጠናከረ ሁኔታ ማስቀጠልና ትግሉን ከዳር ለማድረስ ከምንጊዜውም በላይ ቆርጠው መነሳታቸውን ጠቁመዋል።

ሁሉም የኤርትራ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአሁኑ ወቅት ካለበት አስከፊ ስርዓት ነጻ እስከሚወጣ በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ የህልውና  ትግል በጋራ ለመታገልም በአቋም መግለጫቸው ጥሪ አቀርበዋል።

የኤርትራ ወደብ ከተማ ሂርጊጎ
የኤርትራ ወደብ ከተማ ሂርጊጎ ምስል PETER MARTELL/AFP/Getty Images


የኤርትራ ተቃዋሚ ኀይሎች


 ተስብሳቢዎቹ በዚሁ መግለጫቸው፣ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የደረሱበትን ስምምነት በጋራ እንተገብራለን ብለዋል። በዚህ ስብሰባ ላይ ከተሳተፉት መኻከል፣ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎች እንደሚገኙበት አቶ አብዱ ጠቁመዋል። «በዚህ ስብሰባ ላይ ከፍተኛ የሆኑ የቀይ ባሕር አፋር ወጣቶች ተገኝተዋል። የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎችም ተገኝተዋል። ከቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ ጎን መሆኑን ለእኛም አረጋግጠውልናል።»

 በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ የስደተኞች ካምፖች የሚገኙ የቀይ ባሕር አፋር ስደተኞችን አስመልክተው፣ ተሰብሳቢዎቹ በመግለጫቸው ወደ ሦስተኛ ሀገር የመዘዋወር ዕድል እንዲያገኙ ለሚመለከተው ሁሉ ጥሪ አቀርበዋል።

 አቶ ያሲን አህመድ አብደላ፣ የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን ወክለው ጉባዔው ላይ ለመሣተፍ ከስዊድን ተጋብዘው መምጣታቸውን ገልጸውልናል። ጉባኤው ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳለውም ይናገራሉ። 


ወጣቱ ለስደት ተዳርጓል

እንደ አቶ ያሲን፣ በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ ብዙ ግፍ እየደረሰበት እና እየተሰደደ ያለው ወጣቱ ክፍል ነው። «በአብዛኛው ወጣቱ ተሰዳጅ ነው። አሁን ብዙ ግፍ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ ዋናው ተጠቂው አብዛኛው የቀይ ባሕር አፋር ወይም የኤርትራ ሕዝብ ወጣቱ ነው አብዛኛው። ይህ ክፍል ደግሞ ዛሬ በስደት ላይ ይገኛል።» 

የተነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ደውለን በሰጡን ምላሽ፣ ስለተባለው ሁሉ የሚያውቁት ነገር ስለሌለ፣ አስተያየት ለመስጠት እንደማይችሉ ነው ገልጸዋል።

ታሪኩ ኃይሉ 
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ሽዋዬ ለገሠ