1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞው ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ አረፉ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 6 2011

​​​​​​​የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በ 94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሔርነት ለ12 ዓመታት ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም አገልግለዋል። 

https://p.dw.com/p/3ABG2
Girma Wolde Geiorgis
ምስል DW/T. Getachew

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በ 94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሔርነት ለ12 ዓመታት ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም አገልግለዋል። 

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፕሬዚደንቱ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ከጽሕፈት ቤታቸው በወጣው መረጃ ገልጸዋል። እንዲሁም ጽሕፈት ቤቱ መንግሥታዊ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን የሚያስፈጽም ብሔራዊ ኮሚቴ እንደተቋቋመ እና በቅርቡ አስፈላጊው መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

95 ዓመት ሊሞላቸው ሁለት ሳምንት ገደማ ሲቀራቸው ያረፉት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የሞት ምክንያት በይፋ አልተገለፀም። የቀድሞው ፕሬዚደንት ከዕርሰ ብሄርነት በተጨማሪ ከአጼ ኃይለሥላሴ የአገዛዝ ዘመን አስንስቶ ለግማሽ ምእተ ዓመት በልዩ ልዩ የኃላፊነት ሥራ ያገለገሉ እና ስድስት ቋንቋዎች የሚናገሩ ነበሩ።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ