1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ማክሰኞ፣ የካቲት 26 2011

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ምዕራብ ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከስፍራው የተፈናቀሉ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አለመቻላቸውን  አስታወቁ። እነዚህ ወገኖች  ከስድስት ወራት በፊት በተፈጠረው ችግር ወደ ነቀምት፣ ባሕር ዳር፣ ግልገል በለስ እና ወደ ሎሎችም አካባቢዎች የሸሹ ናቸው።

https://p.dw.com/p/3ETPD
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

«ሠራተኞች ደሞዝ አልተከፈለንም ይላሉ»

በርካቶችን ለመፈናቀል፣ ንብረት መውደም እና ሕይወት መጥፋት የዳረገውን የአካባቢውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በፌደራል የፀጥታ አካላት እና በሁለቱም ክልሎች የሚመራ የእዝ ጣቢያ ወይም ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ይታወሳል። የዕዝ ጣቢያው ከወር በፊት ባወጣው መግለጫ የሰው መፈናቀል ሙሉ በሙሉ መቆሙን፤ በከማሼ እና ሌሎችም አካባቢዎች የተዘጉ መንገዶች መከፈታቸውን ገልጾ ነበር። ሆኖም ግን ከተጠቀሱት አካባቢዎች የተፈናቀሉ የመንግሥት ሠራተኞች አሁንም ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አለመቻላቸን ለDW አስረድተዋል። ዝርዝሩን ከአሶሳ ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ልኮልናል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ