1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔ/ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ

ሐሙስ፣ ኅዳር 13 2011

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞዋ የተቃዋሚ ፓርቲ የአንድነት ሊቀመንበር ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ። በምክር ቤቱ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳን ዛሬ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት በእጩነት ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ናቸው።

https://p.dw.com/p/38inp
Äthiopien Birtukan Midekssa Vorstand Wahlkommission
ምስል DW/G. Giorgis

አዲሷ የብሔ/ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

በምክር ቤቱ በተካሄደው ስነ ስርዓት ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በአራት ተቃዉሞ፣  በሦስት ተአቅቦ እና በአብላጫ የድጋፍ ድምፅ በማግኘት ሹመታቸው ጸድቆላቸው ቃለ መሀላም ፈጽመዋል። ምክር ቤቱ የወይዘሪት ብርቱካን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነትን ሹመት ማጽደቁ በህዝብ ዘንድ አዎንታዊ አስተያየት አግኝቷል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ