1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ የፖለቲካ ቀውስ 

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2011

ረቂቅ ውሉን ያልተቀበሉ የብሪታኒያ ካቢኔ አባላት እና የበታች ሃላፊዎች ትናንት ሥራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸው ውጥረት ውስጥ ላሉት ለብሪታንያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል። ሜይ ትናንት ለፓርላማቸው ባሰሙት ንግግር ውሉ እንዳይፀድቅ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች ይህን ከማድረግ እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/38Omc
England | PK Theresa May
ምስል Reuters/Pool/M. Dunham

የብሪታንያ የፖለቲካ ቀውስ

የአውሮጳ ህብረት እና ብሪታንያ የተስማሙበት ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት የምትወጣበት ፣ረቂቅ የብሬግዚት ረቂቅ ውል በብሪታኒያ የፖለቲካ ቀውስ አስከትሏል። ረቂቅ ውሉን ያልተቀበሉ የብሪታኒያ ካቢኔ አባላት እና የበታች ሃላፊዎች ትናንት ሥራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸው ውጥረት ውስጥ ላሉት ለብሪታንያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል። ሜይ ትናንት ለፓርላማቸው ባሰሙት ንግግር ውሉ እንዳይፀድቅ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች ይህን ከማድረግ እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል። ሜይ ይህን መሰሉ እቋም የብሪታንያ ህዝብ ከአውሮጳ ህብረት ለመውጣት ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚያደናቅፍ ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል። ቀውሱ ለቴሬሳ ሜይ ሥልጣን አስጊ መሆኑ እየተነገረ ነው። ረቂቁ የብሬግዚት ውል በብሪታንያ ያስከተለውን ቀውስ የለንደኑ ወኪላችን በተከታዩ ዘገባው ያስቃኘናል። 


ድልነሳ ጌታነህ


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ