1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቬንዝዌላዉ ተቃዉሞ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲፈቀድ ይጠይቃል

ማክሰኞ፣ የካቲት 5 2011

የቬንዝዌላዉ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ መሪና ራሳቸዉን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሉ የሾሙት ዩአን ጉዋይዶ የቬንዝዌላ መንግሥት የዉጪ ርዳታ  እንዳይገባ ማገዱን « ድምፅ አልባ  ዘር ማጥፋት» በማለት አወገዙት። ጉዋይዶ የሚመሩት ተቃዋሚ ፓርቲ በሃገሪቱ ከተጠራዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ቀደም ሲል የርዳታ ቁሳቁሶች ወደ ለማስገባት እቅድ ይዞ ነበር።

https://p.dw.com/p/3DEXi
DW im Interview mit Juan Guaido in Caracas
ምስል DW

ራሳቸዉን የቬንዝዌላ ፕሬዚደንት ሲሉ የሰየሙት ዩአን ጉአይዶ ለ «DW» በሰጡት ቃለ- ምልልስ ፕሬዚደንት ማዱሮ የሃገሪቱን ሕዝብ ፍላጎት ማስቀደም ይኖርባቸዋል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።  የቬንዝዌላ መንግሥት ተቃዋሚዎች በሃገሪቱ ዛሬ ይደረጋል ተብሎ ለታቀደዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ዝግጅት መድሐኒትና ምግብ እንዲሁም ፤ አንዳንድ የጽዳት መጠበቅያ ቁሳቁሶችን ወደ ሃገሪቱ ለማስገባት ጠይቆ የነበረ ሲሆን ቁሳቁሱ እንዳይገባ የቬንዝዌላ ወታደሮች ኮሎምቢያ ድንበር ላይ አግደዉታል።     

Venezuela Protest & Demonstration gegen Nicolas Maduro in Caracas
ምስል Reuters/A.M. Casares

« ሁሌም ቢሆን የጦር ኃይሉ ርምጃ ሊያስከትለዉ በሚችለዉን ጉዳይ ላይ እናስጠነቅቃለን። የጦር ሃይሉ የሰብዓዊ ቁሳቁሱን ወደ ሃገር እንዲገባ ይፈቅዳል የሚል ግልጽ እምነት ነበረን። ይሁንና ምግብና የሕክምና ቁሳቁሶች ወደ ሃገር እንዳይገባ አግዶአል። ይህ በሰብዓዊነት ላይ ሊፈፀም የተቃጣ የመብት ጥሰት ነዉ። በቬንዝዌላ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ በመድሃኒት እና በምግብ እጥረት ሲሞቱ በሃገሪቱ   ድምፅ አልባ ወይም በድብቅ እየተፈፀመ ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። መንግሥት ሕዝቡ እንዲኖር ራሱን እንዲጠብቅ ፈቃድ አልሰጠዉም። መንግሥት ሕይወታቸዉን ለሚያጡት ሁሉ ተጠያቂ ነዉ። እንደምሳሌ ለመጥቀስ ልዩ የመንግሥት ኃይላት በሳምንቱዉስጥ በተደረገ ተቃዉሞ ከ 70 ሰዎች በላይ ገድለዋል። ቀጥተኛባልሆነ ግድያ ደግሞ፤ በሃገሪቱ ለሚታየዉ የመድሃኒትና የምግብ እጥረት ምንም አይነት መፍትሄ ለማምጣት አይፈልግም» የቬኑዜዌላ መንግሥት መድሐኒትና የሕክምና ቁሳቁስ እንዳይገባ ማገዱን በመቃወም ባለፈዉ እሁድ በአስራዎች የሚቆጠሩ የሕክምና ዶክተሮች አደባባይ ወጥተዉ ነበር።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ