1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የኤርትራ ማዕቀብ መነሳት

ቅዳሜ፣ ኅዳር 8 2011

ይህ አሁን የተነሳው ማዕቀብ እና የተነሳበት ምክንያት እንዲሁም በኤርትራ እና የአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ የሚኖረው አንደምታ ምን ይሆን?

https://p.dw.com/p/38Qrl
UN-Sicherheitsrat in New York | Debatte Sanktionen gegen Eritrea
ምስል picture-alliance/Xinhua News Agency/L. Muzi

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ላለፉት ዘጠኝ አመታት በኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ያነሳ መሆኑን ባለፈው ዕሮብ አስታውቋል። ምክር ቤቱ ኤርትራ አሸባብ የተባለውን ቡድን ትረዳለች በሚል እና ከጅቡቲ ጋርም ባላት የድንበር ውዝግብ ምክንያት እኢአ በ 2009 ዓ ም በተለይ በጦር መሣሪያ ግዥ ማዕቀብ እና በተወሰኑ ባለስልጧኖቿ ላይም የጉዞ እገዳ እንዲደረግ እና የባንክ ሒሳባቸውም እንዳይንቀሳቀስ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው። ይህ አሁን የተነሳው ማዕቀብ እና የተነሳበት ምክንያት እንዲሁም በኤርትራ እና የአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ የሚኖረው አንደምታ የዛሬው የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት የሚዳስሰው ነው።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ