የተሰዳጆች ዕጣ ፈንታ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2010ማስታወቂያ
እግሮቹ በቤልጂግ መዲና ብራስል ጎዳናዎች ላይ ሲመላለሱ አይታክታቸውም፤ አንዳች ግብ አላቸውና። ልቡ ግን በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ኢትዮጵያ ከእናታቸው ጋር የሚገኙት ሁለት ሕጻናት ልጆቹ ጋር ቀርቷል። ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ቀን እስኪሞላ ድረስ የሦስት እና የዓመት ከመንፈቅ ልጆቹ በዓይነ ኅሊናው እየተመላለሱ ናፍቆቱ ቢያስቸግረውም የዕንባ ዘለላውን ከማበስ ውጪ ግን ምንም ማድረግ አይችልም። በእንዲህ ያለ የስደት አዙሪት ውስጥ ካሉት አንዱን ኢትዮጵያዊ ወጣት እዛው ብራስልስ ውስጥ አነጋግሮት ዳግማዊ ሲሳይ ለዕለቱ አውሮጳ እና ጀርመን መሰናዶ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል።
ዳግማዊ ሲሳይ
ሸዋዬ ለገሠ