1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ አንድ መምጣት 

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2010

አምስት የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠናክረዉ አዲስ በተከፈተዉ የፖለቲካ ምኅዳር የተወሰነ የፖለቲካ ፍልስፍናን በማራመድ መስመር ሊይዙ ይገባል በማለት በመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ጽ/ቤት ዉስጥ መግለጫ ሰጡ። መንግሥት የኢንጂኔር ስመኘዉ በቀለ አሟሟት በአስቸኳይ አጣርቶ ይፋ እንዲያደርግም አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/32JgM
Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Flash-Galerie
ምስል Solomon Mengist

መንግሥት የኢንጂኔር ስመኘዉ በቀለ አሟሟትን በአስቸኳይ እንዲያጣራ አሳስበዋል

መግለጫ የሰጡት ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት« መኢአድ » የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ «ኢራፓ »  ኢትዮጵያ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ  «ኢዴፓ» የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት «ኢሕዴኅ»ን እና ሰማያዊ ፓርቲ ናቸዉ። ፓርቲዎጡ በሰጡት መግለጫ ከተቃዋሚ ፓርቲ ብዛት ይልቅ በተወሰነ የፖለቲካ ፍልስፍና ዉስጥ አንድ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ ሌላ መንግሥት የሕዳሲ ግድብ ዋና ተጠሪ የኢንጂኔር ስመኘዉ በቀለ አሟሟት በአስቸኳይ አጣርቶ ይፋ እንዲያደርግም አሳስበዋል። በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የነበረዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዘገባዉን ልኮልናል። 


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ