1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተባረሩ መምህራን በጊብሰን አካደሚ አንጻር ያሰሙት ወቀሳ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 9 2010

በአዲስ አበባ የሚገኝ ጊብሰን አካዳሚ የተባለ የግል ትምህርት ቤት መምህራን አላግባብ ከስራ መባረራቸውን  ተናገሩ። ከተለያዩ የትምህርት ቤቱ  ቅርንጫፎች የተባረሩት አስር መምህራን የትምህርት ስርዓት ጥራት እንዲጠበቅ እና የሰራተኞችም መብት እንዲከበር መጠየቃቸው ለመባረራቸው ምክንያት እንደሆነ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3393x
Symbolbild Lehrerstreik
ምስል picture-alliance/dpa/J. Kalaene

«የት/ቤቱ አስተዳደር መምህራኑ ያነሷቸውን መኖራቸው በሌላ አካል የተረጋገጡትን ችግሮች ማመን አልፈለገም።»

የተባረሩት መምህራን አክለው እንዳሉትም፣ እነሱ እና ባልደረቦቻቸው ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር ዛቻ፣ ማስፈራራት እና የደሞዝ ቅጣትም ይደርስባቸዋል። መምህራኑ በጊብሰን አካዳሚ አንጻር ያነሷቸውን ችግሮች የአጠቃላይ የአዲስ አበባ የትምህርት ጥራት  እና ሬጉላተሪ ኤጀንሲም መመልከቱንም አረጋግጧል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ