1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትልቆቹ የጀርመን ፖለቲካ ፓርቲዎች እጣ ፈንታ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2011

በጀርመን ፌዴራዊ የሄሰን ግዛት የፊታችን እሁድ ምክር ቤታዊ ምርጫ ይካሄዳል። ሁለቱ ትልቆቹ ፓርቲዎች፣ ማለትም፣ የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት፣ በምህጻሩ ሴ ዴ ኡ እና የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ፣ በምህጻሩ ኤስ ፔ ዴ  በዚሁ ምርጫ ብዙ የመራጭ ድምፅ እንደሚያጡ የህዝብ አስተያየት መመዘኛዎች ጠቁመዋል።

https://p.dw.com/p/372zF
Volker Bouffier und Thorsten Schäfer-Gümbel
ምስል picture-alliance/dpa

የትልቆቹ የጀርመን ፖለቲካ ፓርቲዎች እጣ ፈንታ

ከሁለት ሳምንትም በፊት በሌላው ፌዴራዊ ግዛት ባየር  በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ  የክርስትያን ሶሻል ህብረት፣ በምህጻሩ ሴ ኤስ ኡ እና ኤስ ፔ ዴ ድጋፍ የሚሰጣቸው ብዙ መራጭ ህዝብ አላገኙም። በአንጻራቸው ትንንሾቹ ፓርቲዎች ቀንቷቸዋል።በሀገሪቱ በአሁኑ ጊዜ የሚሰራበት የፖለቲካ ውክልና  ጊዜው ያለፈበት እንደሆነ የሚናገሩት የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ትልቆቹ ፓርቲዎች የመራጭ ድምፅ እያጡ የመጡበት ሁኔታ መግቻ የሚገኝለት አይመስልም። ትልልቆቹ የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገኙበት አዳጋች ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ