1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የትራምፕ እና የፍራንሲስ ዉይይት

ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2009

ከሪያድ በየእሩሳሌም አድርገዉ ትናንት ሮም-ኢጣሊያ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ቫቲካን ዉስጥ ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/2dX0O
Vatikan Donald Trump trifft Papst Franziskus
ምስል Reuters/A. Tarantino

MM T/ (Beri.Rome) Trump in Rome - MP3-Stereo

ከካቲሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ከተነጋገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትነታቸዉን በመላዉ ዓለም ሰላም እንዲስፋፋ ግፊት ለማድረግ እንደሚጠቀሙበት ዶናልድ ትራምፕ አመለከቱ። ልዩነታቸዉን በሆዳቸዉ አድርገዉ ፊትለፊት የተገናኙት ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንሲስ እና ትራምፕ፤ የአካባቢ ጥበቃ፣ ስደተኞችንና ድሀዉን ማኅበረሰብ ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል። በዓለም ላይ ሰላምን ለማስፈን የነበራቸዉ አቋም ይበልጥ ቁርጠኛ ሆኖ የቫቲካን ጉብኝታቸዉን ማጠናቀቃቸዉን ያመለከቱት ትራምፕ ፤ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳቱ የተናገሩትን እንደማይዘነጉት በትዊተር አስፍረዋል ። ዓለም አቀፍ የሰላም ምልክት የሆነ ሜዳሊያ ለትራምፕ ያበረከቱት የካቶሊካዉያን የሃይማኖት አባት በበኩላቸዉ፤ ለሰላም መሳሪያ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።  

ሁለቱ መሪዎች ለሰላሳ ደቂቃ ያክል በዝግ ያደረጉት ዉይይት የቫቲካንና የዩናይትድ ስቴትስን ግንኙነት፤ የመካከለኛዉ ምሥራቅን ቀዉስና የኃይማኖት ነፃነትን የቃኘ ነዉ ከመባሉ ሌላ ዝርዝሩ አልተገለጠም። ሁለቱ መሪዎች በይፋ የሰጡት መግለጫም የለም።ፕ ሬዝደንት ትራም በሮም ቆይታቸዉ ከኢጣሊያ ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ሚንስትር ጋርም ተነጋግረዉ ነበር። የጣሊያን ጉብኝታቸዉን ያጠናቀቁት ትራምፕ ልዩ ስሜት አሳደሩብኝ ያሏቸዉን ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንሲስን እያወደሱ ነገ በሚካሄደዉ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ብራስልስ ገብተዋል።  

ተክለ እግዚ ገብረየሱስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ