1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ እጥረት በድሬዳዋና ሀረር ከተሞች

ሰኞ፣ ጥር 13 2011

የድሬዳዋ እና ሀረር ከተሞች ነዋሪዎች ካለፉት ቀናት ወዲህ የነዳጅ እጥረት ገጥሟቸዋል። ከዚሁ ጎንም ያለውን ነዳጅ በሚገባ ማድረስ አለመቻሉም ችግራቸውን ይበልጡን እንዳባባሰው DW ያነጋገራቸው ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3Bufx
Äthiopien Schlange für Treibstoff in Dire Dawa
ምስል DW/M. Teklu

የነዳጅ እጥረት በድሬ ዳዋ እና ሀረር ከተሞች

ወደ ሀገሪቱ ለሚገባው ነዳጅ አንድ አማራጭ የሆነው የጅቡቲ ወደብ አቅራቢያ መገኘቷ ምንም ያልፈየደላት ድሬደዋ ሰሞኑን በከተማዋ በተከሰተ የነዳጅ አቅርቦት በተለይም የቤንዚን እጦት ፈተና ውስጥ ሰንብታለች ፡፡ ይህ የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሰሞኑን በተገኘሁበት ሀረር ከተማም ተመሳሳይ ገፅታ እንዳለው ተመልክቻለሁ ፡፡ ተሽከርካሪዎች መሰለፍ እጣ ፈንታቸው የሆነ እስኪመስል በከተሞቹ ዛሬ ነዳጅ አለው በተባለ ማደያ በረድፍ ተደርድረው ማየት ከመለመዱ ባለፈ ፤ በአቅርቦቱ የተቸገሩ አሽከርካሪዎች በከተማው ከማደያ ውጭ ካሉ ነጋዴዎች በጀርካን ገዝቶ ማንቀሳቀስ መደበኛ ስራቸው ሆኗል ፡፡ በሁለቱ ከተሞች ከወትሮም ለየት ባለ መልኩ እየታየ ያለውን የነዳጅ እጥረት በሚመለከት ያነጋገርኳቸው አሽከርካሪዎች በማደያዎች የነዳጅ እጥረት መኖር ብቻ ሳይሆን ያለውን በተገቢው መንገድ ለተጠቃሚው የማዳረስ ችግር መኖሩን ገልፀዋል ፡፡በከተሞቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚው የብዞዎቹ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ እጦት መቆም ባስከተለው የአገልግሎት እጥረት መሰቃየት አሊያም በለስ ቀንቷቸው ስራ ላይ ለሚገኙት ከታሪፍ ውጭ ከፍሎ ለመስተናገድ ተገዷል፡፡ ይህም በህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖው ትልቅ ነው ይላሉ ፡፡በሁለቱም ከተሞች ቤንዚን በማደያ ከሚሸጥበት ዋጋ መግዛት ባለመቻሉ በጀሪካን ከሚሸጡ ግለሰቦች አንዱን ሊትር እስከ ሀያ አምስት ብር መግዛት ቀዳሚ ምርጫ እየሆነ መጥቷል ፡፡ ለዚህ ደግሞ የመቆጣጠርና በህገወጥ አሰራር ላይ እርምጃ የመውሰድ ሀላፊነት ያለበት የመንግስት ተቋም ስራውን በአግባቡ ባለመስራቱ የመጣ ችግር መሆኑን ይገልፃሉ ፡፡ተጠቃሚው የሚያነሳውን ይህን ቅሬታ መሰረት በማድረግ ያነጋገርኳቸው ሀላፊዎች አስተያየት ተመሳሳይ ነው የድሬደዋ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላተሪ  ዳይሬክቶሬት ሀላፊ አቶ አህመድ አብደላ የሚያነሱትን እናድምጥ ፡፡ተገልጋዩ በእናንተ በኩል መስራት ያለባችሁን የቁጥጥር ስራ መስራት ባለመቻላቸው የመጣ ነው በሚል የሚያነሳውን ቅሬታ ለሀላፊው አንስቼላቸው ነበር ፡፡ከሁለት ቀናት በፊት በድሬደዋ ከማደያ ባለቤቶች ጋር ውይይት ተካሂዶ ነበር፣ ዓላማው እርምት እንወስዳለን የሚል ማስጠንቀቅያ መስጠት ነበር፣ ይሁን እንጂ በአግባቡ ስራቸውን ባልሰሩ ማደያዎች ላይ ፍቃድ እስከመሰረዝ የሚያስችል የህግ ስልጣንና ሀላፊነት ቢኖረውም ዛሬም ይህ ነው የሚባል ርምጃ ሲወስድ አለመታየት መፍትሄውን ሳያርቅ አይቀርም የሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ።

Äthiopien Dire Dawa City
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

መሳይ ተክሉ

አርያም ተክሌ

እሸቴ በቀለ