1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኒጀር ወታደራዊ ጁንታ የሀገሪቱን የአየር ክልል ዘጋ

ሰኞ፣ ነሐሴ 1 2015

የኒጀር ወታደራዊ ጁንታ የሀገሪቱ የአየር ክልል መዘጋቱን አስታወቀ። ወታደራዊ ጁንታዉ ይህን ያደረገዉ ኤኮዋስ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ለመፈፀም ያስቀመጠዉ ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ ነዉ። የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት የኤኮኖሚ ማሕበረሰብ «ECOWAS» ኒጀርን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/4UsFA
Niger, Niamey | Kundgebung von Anhänger der Putschisten
ምስል Mahamadou Hamidou/REUTERS

የኒጀር ወታደራዊ ጁንታ የሀገሪቱ የአየር ክልል መዘጋቱን አስታወቀ። ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት የኒጀርን ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙምን ከስልጣን አዉርዶ መንበሩን የተቆጣጠረዉ የኒጀሩ ወታደራዊ ጁንታ የሃገሪቱን የአየር ክልል መዝጋቱን ያስታወቀዉ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት የኤኮኖሚ ማሕበረሰብ «ECOWAS» የኒዠርን ዴሞክራሲ ለመመለስ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚፈፅም የያዘዉን ቀነ ቀጠሮ ማብቃቱን ተከትሎ ነው።
ኤኮዋስ የኒጀርን ስልጣን በጉልበት ይዞ የሚገኘዉ ወታደራዊ ቡድን አስርዋቸዉ የሚገኙትን ፕሬዚዳንት ወደ ስልጣን እንዲመልስ ሲል እስከ ትናንት እሁድ ድረስ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር። በጎርጎረሳዉያኑ በ 2020 እና 2022 ዓ.ም ወታደራዊ ኃይላት በጉልበት ሥልጣን የያዙባቸዉ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ዛሬ ሰኞ ከኒጀር ጋር ለመተባበራቸዉ የጋራ ልዑካን በመላክ አጋርነታቸዉን እንደሚያሳዩ ገልፀዉም ነበር። የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት የኤኮኖሚ ማሕበረሰብ «ECOWAS» ኒጀርን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ኒጀር በዓለም ላይ ትልቋ የዩራኒየም አምራች ሃገር ናት። ከዚህ ሌላ ኒጀር  ጽንፈኝነትን በመዋጋት ረገድ ቁልፍ አጋር ተደርጋም ተወስዳለች። ይሁን እንጂ ከአስር ቀናት በፊት በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ኒጀር እርዳታ ለማግኘት ወደ ሩሲያ ፊትዋን ታዞራለች የሚል ግምት እንዳለተነግሯል።  
 

አዜብ ታደሰ 

እሸt በቀለ