1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አቋም

ማክሰኞ፣ ሰኔ 19 2010

አርበኞች ግንቦት ሰባት የፍትሕ፤ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተያዘዉን የለዉጥ እርምጃ ለመቀልበስ የሚያሴሩ ኃይላትን ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ።

https://p.dw.com/p/30L5h
Europaparlament Sitzung mit Ana Gomes & Berhanu Nega & Andergachew Tsegue
ምስል Ana Gomes

«የሚወስዱት እርምጃ እራሳቸዉን የሚያጠፋ ነዉ»

የንቅናቄዉ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሐኑ ነጋ ዛሬ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት ለዉጡን ለመቀልበስ የሚሸረበዉን ሴራ ለማክሸፍ ድርጅታቸዉ አበክሮ ይታገላል። ዶክተር ብርሐኑ «በቀድሞዉ ሥርዓት የሚያጋብሱት ጥቅም የቀረባቸዉ ያሏቸዉ ኃይላት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡን ለማወክ የሚያደርጉት ሙከራ እና የሚወስዱት እርምጃ እራሳቸዉን የሚያጠፋ ነዉ ብለውታል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለዉጡን ከአደጋ ለማዳን አስፈላጊዉን ሁሉ እንደሚያደርግም ዶክተር ብርሐኑ አስታዉቀዋል። ዛሬ ብራስልስ ቤልጂግ የሚገኙትን ዶክተር ብርሐኑን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሮአቸዋል። የመጀመሪያዉ ጥያቄ የብራስልስ ጉብኝታቸዉን አላማ የሚመለከት ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ