1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሻጎዳ የኃይ ማመንጫ ሥራ አቁሟል

ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2011

የአሻጎዳ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተቋም በሙሉ አቅሙ ኃይል ማመንጨት ካቋረጠ ከዓመት ከመንፈቅ እንደበለጠዉ የዓይን ምስክሮችና ባለሙያዎች አጋላጡ።ከስድት ዓመት በፊት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ የተባለዉ ተቋም በተመረቀበት ወቅት 120 ሜጋዋት የኤልክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ነበር

https://p.dw.com/p/3IuEG
Äthiopien Windenergie in Ashegoda
ምስል DW/M. Haileselassie

የአሻጎዳ ኃይል ማመንጫ አገልግሎት አይሰጥም

 ትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌ አጠገብ የሚገኘዉ የአሻጎዳ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተቋም በሙሉ አቅሙ ኃይል ማመንጨት ካቋረጠ ከዓመት ከመንፈቅ እንደበለጠዉ የዓይን ምስክሮችና ባለሙያዎች አጋላጡ።ከስድት ዓመት በፊት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ የተባለዉ ተቋም በተመረቀበት ወቅት 120 ሜጋዋት የኤልክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ነበር።የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል መስሪያ ቤት አገልጎሎት ያቋረጡ ተቋማትን ከማስጠገን ይልቅ የኤሌክትሪክ ኃይል በቁነና (በፈረቃ) ለማደል ወስኗል።የአሻጎዳዉን የኤሌክትሪክ ተቋም የጎበኘዉ የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ እንደዘገበዉ ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚገባቸዉ አብዛኞቹ የተቋሙ መዘዉሮች (ተርባዮኖች) አይሰሩም።

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋአለም ወልደየስ