1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት የመሪዎች ጉባዔ 

ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2011

የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች እና ተወካዮቻቸዉ በኅብረቱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት ተወያዩ። ቱስክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ የሽግግሩ ጊዜ ወደ ሁለት ዓመት ሊሆን እንደሚችል ቀደም ሲል፣ መጥቀሳቸውን አስታውሰዋል።

https://p.dw.com/p/36nTE
Belgien | Beginn EU-Gipfel mit Beratungen zum Brexit
ምስል Reuters/Y. Herman

በብሪግዚት፤ በደኅንነትና በስደተኞች ጉዳይ ተወያይተዋል

የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች እና ተወካዮቻቸዉ በኅብረቱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት ተወያዩ። የመወያያዉ አጀንዳ በተለይ ብሬግዚት ማለትም ብሪታንያ ከኅብረቱ የምትወጣበትን መንገድ ለማስተካከልና፤ ብሪታንያ ከኅብረቱ ጋር ትፈጽማለች ስለተባሉት ዉሎች ላይ መክረዋል ከዚህ በተጨማሪ በምርቻ ጊዜ ስለሚደርስ የሳይበር ማለትም ጥቃት ማለትም በኢንተርኔት በኩል ሊደርስ የሚችል የመረጃ ስርቆቶችን በማስወገዱ ረገድና፤ ሜዲተራንያን ባኅርን አቋርጠዉ የሚመጡ ስደተኞች ላይ አተኮሮ ነዉ የዋለዉ። ብሪታንያ ከአውሮጳ ኅብረት ከወጣች በኋላ ተጨማሪ የሽግግር ጊዜ እንዲሰጣት ለአውሮጳ ኅብረት ለምታቀርበው ማንኛውም ጥያቄ  የኅብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች አዎንታዊ መልስ እንደሚሰጡ እርግጠኛ መሆናቸውን የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ዶናልድ ቱስክ  አስታወቁ።  ቱስክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ የሽግግሩ ጊዜ ወደ ሁለት ዓመት ሊሆን እንደሚችል ቀደም ሲል፣ መጥቀሳቸውን አስታውሰው፣ 21  ወር የሆነውን የሽግግር ጊዜ ስለማራዘሙ ጉዳይ በኅብረቱ ጉባዔ ወቅት አለመነሳቱን አመልክተዋል። ጉባኤዉን የተከታተለዉ የብረስልሱ ወኪላችን ስለጉባኤዉ በስልክ ገልፆልናል። 


ገበያዉ ንጉዜ 
አዜብ ታደሰ