1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት እና ስደት

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2011

ሃያ ስምንቱ የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ትናንት እና ዛሬ በኦስትሪያዋ ሳልስቡርግ ከተማ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ አካሂደዋል። መደበኛ ያልሆኑ የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ስብሰባዎች ውሳኔዎች የማይተላለፉባቸው ይሁኑ እንጂ አስቸጋሪ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ መሪዎቹ በጥልቀት በመወያየት ልዩነቶቻቸውን የሚያጠቡባቸው እና ስምምነት የሚፈጥሩባቸው ናቸው።

https://p.dw.com/p/35FpV
Österreich, Salzburg, Gipfel
ምስል picture-alliance/Y.Pingfan

ኢመደበኛው ጉባኤ

ትናንና እና ዛሬ በተካሄደው የመሪዎቹ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባም በአሁኑ ወቅት የኅብረቱ አስቸጋሪ አጀንዳዎች በሆኑት የስደተኞች የውስጥ የፀጥታ ቁጥጥር እና የብሬግዚት ጉዳዮች መክረዋል። ውሳኔ ለማሳለፍ ግን የሚቀጥለውን የጥቅምቱን ጉባኤ ይጠብቃሉ። ከብራስልስ ገበያው ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ