1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ የንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እቅድ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 29 2010

የአዲስ አበባ የንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የአባላቱን ፍላጎት  ለማርካት ተቋማዊ ለውጥ ለማስገኘት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። አንድ የምክር ቤቱ ባለስልጣን እንደገለጹት፣  ምክር ቤቱ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች እያደገ ከመጣው የንግዱ ማህበረሰብ  ፍላጎት ጋር ለማጣጣም የአመራር አባላት ለውጥ ያደርጋል። 

https://p.dw.com/p/34Hdl
Karte Äthiopien englisch

የአዲስ አበባ የንግድ ም/ቤት

በቀጣዩ ጥቅምት፣ 2011 ዓም ጠቅላላ ጉባዔ የሚያካሂደው ምክር ቤት ራዕይ ያላቸው ባለሙያዎችን በአመራር ቦታ በማስቀመጥ የምክር ቤቱን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ማሰቡን አስረድቷል። 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 
አርያም ተክሌ   
አዜብ ታደሰ