1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሕአዴግ ጉባኤ

ረቡዕ፣ መስከረም 23 2011

የዘንድሮዉ ጉባኤ  27 ዓመት በዘለቀዉ የኢሕአዴግ አገዛዝ፣ ግንባሩ ለየት ያለ ያመራር እና የፖለቲካ ለዉጥ ባደረገበት እና ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ የጎሳ ግጭቶች በሺ የሚቆጠሩ ዜጎችዋ በሚገደሉ እና በሚፈናቀሉበት ወቅት የተደረገ ነዉ።

https://p.dw.com/p/35vTa
Äthiopien Parteikongress 11. Kongress der Revolutionären Demokratischen Front des äthiopischen Volkes
ምስል DW/Yohannes Geberegziabeher

(Beri.Hawassa) EPRDF Congress - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) 11ኛ ጉባኤ ዛሬ ሐዋሳ ዉስጥ ተጀምሯል። የዘንድሮዉ ጉባኤ  27 ዓመት በዘለቀዉ የኢሕአዴግ አገዛዝ፣ ግንባሩ ለየት ያለ ያመራር እና የፖለቲካ ለዉጥ ባደረገበት እና ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ የጎሳ ግጭቶች በሺ የሚቆጠሩ ዜጎችዋ በሚገደሉ እና በሚፈናቀሉበት ወቅት የተደረገ ነዉ። አዲሱ የግንባሩ ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለጉባኤተኞች እንደገሩትም ግጭት ጥፋቱ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚጎዳ ነዉ። በተለይ ከደቡብ፤ ከኦሮሞ እና ከአማራ ፓርቲዎች አዳዲስ ፖለቲከኞች የተቀየጡበት ጉባኤ እስከፊታችን አርብ  በዝግ ይመክራል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ