1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 10 2010

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ባለ አምስት ኮከብ ምልክት ያለው የአሁኑ ሰንደቅ ዓላማ አወዛጋቢ በመሆኑ ምንም ምልክት የሌለው ሰንደቅ ዓላማ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሆን ጠይቋል ።

https://p.dw.com/p/31ano
[No title]
ምስል DW/G.Tedla

የሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን በሚመለከት መንግሥት የህዝብን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ።  በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ባለ አምስት ኮከብ ምልክት ያለው የአሁኑ ሰንደቅ ዓላማ አወዛጋቢ በመሆኑ ምንም ምልክት የሌለው ሰንደቅ ዓላማ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሆን ጠይቋል ። የፓርቲው አመራሮች በቀደሙት መንግሥታት  ይሰራበት የነበረው ሰንደቅ ዓላማ እንዲመለስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙም በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። መግለጫውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሎታል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ