1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርቀ ሰላም ውይይት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 10 2010

ከቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ የተወከሉ ሦስት ብጹአን አባቶች ከነገ በስተያ ለዚሁ የእርቅ ውይይት አሜሪካን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በእርቅ ይጠናቀቃል ተብሎ ተስፋ በተጣለበት በዚህ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ይገኛሉ ተብሏል።

https://p.dw.com/p/31aN5
Sitz des Patriarchen der äthiopisch-orthodoxen Kirche in Addis Abeba
ምስል DW

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእርቀ ሰላም ውይይት

በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ  በዚህ ሳምንት ይጀመራል ተብሎ ለሚጠበቀው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጋር ለሚደረገው እርቀ ሰላም  ሦስት ብጹአን አባቶችን መምረጡን አስታውቋል። ከቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ የተወከሉ ሦስት ብጹአን አባቶች ከነገ በስተያ ለዚሁ የእርቅ ውይይት አሜሪካን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በእርቅ ይጠናቀቃል ተብሎ ተስፋ በተጣለበት በዚህ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ይገኛሉ ተብሏል። ዶቼቬለ ስለጉዳዩ ያነጋገራቸው በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ፓትሪያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ በዚህ ውይይት የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት እውን ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ