1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እርቀ ሰላም በኢ/ኦ/ተ/ቤ

እሑድ፣ ሐምሌ 29 2010

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለ27 ዓመታት ከፋፍሏት የኖረውን ልዩነት አስወግዳ አንድነቷን ከሰሞኑ አውጃለች። ለዚህ መገለጫም በስደት ለ26 ዓመታት በአሜሪካን ሀገር የቆዩት አራተኛው ፓትሪያርክ እና በውጭ የተቋቋመው የሲኖዶስ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

https://p.dw.com/p/32bd8
Äthiopien Begrüßung des Exil-Patriarchen am Flughafen von Addis Abeba
ምስል DW/Yohannes G/Egziabhare

ውይይት፦የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እርቅና ተግዳሮት

ለረዥም ዓመታት በይፋም ምስጢርም ልዩነቱን አቀራርቦ ሰላም አንድነቷን ለመመለስ የተካሄደው ጥረት ፍሬ ሳያሳይ ከርሟል። የሃይማኖት አባቶቹ እንደሚገልፁት በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሳቢያ በተከተለው የቀኖና ጥሰት ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትከፋፈል ተከታዮቿንም በየፈርጁ ከፋፍሎ ቆይቷል። ከሁለት ሲኖዶስ ወደ አንድነት መመለሱ እና የተፈጠረው እርቀ ሰላም አንድ ነገር ሆኖ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው ክፍፍል የፈጠራቸው ክፍተቶች ቀጣይ ተግዳሮት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚገምቱ ጥቂት አይደሉም። ዶይቼ ቬለ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት አባቶች በጉዳዩ ላይ አወያይቷል። ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ