1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አቋም

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 18 2010

የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ እንዳሉት ኢትዮጵያን የጎበኙት የኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊ ዘይድ ረዓድ ሁሴይ እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፅሕፈት ቤቱ እንዲከፈት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

https://p.dw.com/p/2wjHk
Äthiopien Sprecher Außenministerium Meless Alem
ምስል DW/Getachew Tedla Hailegiorgis

(Beri.AA) EMoF Press conference - MP3-Stereo

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠብአዊ መብት ኮሚሽን የአስራ-ሰባት የአፍሪቃ ሐገራትን የሰብአዊ መብት ይዞታ የሚከታተልበት ፅሕፈት ቤት አዲስ አበባ ዉስጥ ሊከፍት ነዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ እንዳሉት ኢትዮጵያን የጎበኙት የኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊ ዘይድ ረዓድ ሁሴይ እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፅሕፈት ቤቱ እንዲከፈት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።ቃል አቀባዩ በሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ሶማሊያ የሠፈረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሰራዊት በበጀት እጥረት ምክንያት ወደየሐገሩ ይመለስ የሚለዉን ሐሳብ ኢትዮጵያ አትቀበለዉም።  

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ