1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያኑ ፓስፖርት የማግኘት ፈተና

ዓርብ፣ ሰኔ 7 2011

የኢትዮጵያውያን ፓስፖርት ፈላጊዎች 45 ቀናት መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ ቀደም የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ማመልከቻ በቀረበ በሦስት ቀናት ውስጥ ፓስፖርት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እንዲራዘም ሆኗል።

https://p.dw.com/p/3KTyD
Äthiopischer Pass
ምስል DW/E. B. Tekle

የኢትዮጵያውያኑ ፓስፖርት የማግኘት ፈተና

የኢትዮጵያውያን ፓስፖርት ፈላጊዎች 45 ቀናት መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ ቀደም የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ማመልከቻ በቀረበ በሦስት ቀናት ውስጥ ፓስፖርት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እንዲራዘም ሆኗል። ረዥም ሰልፍ ወደ ሚታይበት የአዲስ አበባው የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ያቀኑ አገልግሎት ፈላጊዎች ለስርቆት መጋለጣቸውን ጭምር ይናገራሉ። በአስር ቅርንጫፎች አገልግሎት የሚሰጠው የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ደቡብ ሱዳናውያን እና ኤርትራውያንን ጨምሮ ፓስፖርት ለማይገባቸው ሰዎች ጭምር እየተሰጠ እንደ ሆነ ገልጿል። ሰለሞን ሙጬ ተጨማሪ ዘገባ አለው። 
 ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ