1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንተርኔት መቆራረጥ የድርጅቶችን ሥራ እያስተጓጎለ ነዉ 

ማክሰኞ፣ ሰኔ 11 2011

ፕራይም የተባሉ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ድርጅቶች እንዲህ ያለው እርምጃ እንደ ሃገር የምንጋራው የመሠረተ ልማት ችግር ቢሆንም በእንጭጭ ደረጃ ላይ ያለውን የ «IT» እና የኢንተርኔት ዘርፍ ልማት የሚጎትት ነው ብለውታል። የአገልግሎቱን መቆራረጥ ምክንያት በግልጽ ያሳወቀ የመንግስት አካል አለመኖሩም ሌላ ችግር እንደሆነባቸው ነው ድርጅቶቹ ያስታወቁት።

https://p.dw.com/p/3KatG
Symbolbild Urheberrecht im Internet | Youtube-Upload
ምስል picture-alliance/dpa/R. Knipping

ኢንተርኔትን የሚያቀርቡ የግል ኩባንያዎች አለመኖራቸው የችግሩ ምክንያት ነዉ

ሳናውቀው ፣ ሳይነገረንና ዝግጅት ሳናደርግ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተቆራረጠ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት ከፍተኛ ጫና አሳድሮብናል በማለት በሶፍትዌር ማልማት ላይ የተሰማሩ ትልልቅ ድርጅቶች አማረሩ። ዶቼ ቬለ «DW» ያነጋገራቸው ሲኔት እና ፕራይም የተባሉ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ድርጅቶች እንዲህ ያለው እርምጃ እንደ ሃገር የምንጋራው የመሰረተ ልማት ችግር ቢሆንም በእንጭጭ ላይ ያለውን የIT እና የኢንተርኔት ዘርፍ ልማት የሚጎትት ነው ብለውታል። የአገልግሎቱን መቆራረጥ ምክንያት በግልጽ ያሳወቀ የመንግስት አካል አለመኖሩም ሌላ ችግር እንደሆነባቸው ነው ድርጅቶቹ ያስታወቁት። የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያቀርቡ የግል የቴሌኮም ኩባንያዎች አለመኖራቸው ለእንዲህ ያለው ወቅትን ጠብቀው ለሚደረጉ የአገልግሎት መቆራረጦች ምክንያት መሆኑንም አመልክተዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ