1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ የባሕል የሙዚቃ ቡድን በባሕር ዳር

እሑድ፣ የካቲት 10 2011

የኤርትራ የባሕል የሙዚቃ ቡድን ቅዳሜ የካቲት 9 ቀን፣ 2011 ዓ.ም በባሕር ዳር የሙዚቃ ዝግጅቱን አቅርቧል፡፡ በዝግጅቱ የተገኙት በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር አረአያ ደስታ የጥላቻ ጤዛ ተራግፏል ሲሉ፤ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ባለፉት ዓመታት የተፈፀሙ ስህተቶች መሪዎች በተከተሉት የተሳሳተ አቅጣጫ ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3DYEc
Äthiopien Eritreische traditionelle Musikshow in Bahir Dar
ምስል Alemnew Mekonnen

«የጥላቻ ጤዛ ተራግፏል»

የኤርትራ የባሕል የሙዚቃ ቡድን ትናንት በባሕር ዳር የሙዚቃ ዝግጅቱን አቅርቧል፡፡ በዝግጅቱ ላ የተገኙት በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር አረአያ ደስታ እንዳሉት የጥላቻ ጤዛ ተራግፏል፡፡ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት የተፈፀሙ ስህተቶች መሪዎች በተከተሉት የተሳሳተ አቅጣጫ ነው ብለዋል፡፡

60 የሚጠጉ የዘመናዊና ባሕላዊ የሙዚቃ አባላትን ያቀፈው የኤርትራ የሙዚቃ ልዑክ ባሕርዳር የገባው ባለፈው አርብ ነበር፡፡ የሙዚቃ ቡድኑ አባላት በባሕር ዳርና አካባቢው ያሉ የልማት መዳረሻዎችን ጎብኝቷል፡፡የሙዚቀ ቡድኑ የባሕር ዳር ዝግጅቱን አጠናቅቆ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡ ተመሳሳይ የሙዚቃ ትርኢቶችን በአዳማ፣ በሐዋሳና በአዲስ አበባ እንደሚያደርግም ታውቋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ