1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ ከማትተባባር መዝገብ ተሰረዘች

ዓርብ፣ ግንቦት 23 2011

በዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ባለስልጣናት እንደሚሉት ኤርትራ እንደ አሜሪካ «ጠላት» ከተፈረጀችበት መዝገብ የተሰረዘችዉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከጎረቤቶቿ ጋር ሠላም በማዉረዷ ነዉ

https://p.dw.com/p/3JYl2
Symbolbild USA Außenministerium Logo Siegel
ምስል AP

ኤርትራ ለፀረ-ሽብር ከማይተባበሩ ዝርዝር ተሰረዘች


ዩናይትድ ስቴትስ በፀረ-ሽብር ዘመቻ «የማይተባበሩ» ከምትላቸዉ መንግስታት ዝርዝር ዉስጥ ኤርትራን በያዝነዉ ሳምንት ሰርዛለች።በዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ባለስልጣናት እንደሚሉት ኤርትራ እንደ አሜሪካ «ጠላት» ከተፈረጀችበት መዝገብ የተሰረዘችዉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከጎረቤቶቿ ጋር ሠላም በማዉረዷ ነዉ።በኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት እጥራለሁ የሚለዉ አንድ የኤርትራዉያን ዲያስፖራ ማሕበር ግን የአሜሪካ ዉሳኔም ሆነ በኤርትራ ላይ ተጥሎ የበረዉ ማዕቀብ መነሳት ለኤርትራ ሕዝብ የሚጠቅመዉ የለም ባይ ነዉ።

 መክብብ ሸዋ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ