1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራውያን ሰልፍ እና ጥያቄ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት ፍራንክፈርት በኮሜርስ ባንክ አሬና ስታዲየም ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ጋር ሲነጋገሩ ከስታድየሙ ውጭ ደግሞ ኤርትራውያን ሰልፍ አካሂደው ነበር።

https://p.dw.com/p/37Wvn
Frankfurt Demonstration Eritrea
ምስል DW/H. Tiruneh

«በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መሪዎች መካከል የተደረገው ስምምነት ይፋ ይሁን»

 በጀርመን ሀገር ነዋሪዎች መሆናቸውን የገለጹት ኤርትራውያን ሰልፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ለመቃወም ሳይሆን የሀገራቸው ሕዝብ ከኤርትራ ፕሬዝደንት ጋር ያደረጓቸውን ስምምነቶችም ምንነት ማወቅ እንደሚፈልግ ለማሳሰብ እንደሆነ አመልክተዋል። ሕዝብ ያልተሳተፈበት ማንኛውም ስምምነትም ውጤት ሊኖረው እንደማይችል ያሳሰቡት ሰልፉን ያደረጉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዉያን በኤርትራ የታሰሩ እንዲፈቱ፤ የመናገር ነጻነት እንዲኖር እና ፍትህ እንዲመጣም ጠይቀዋል። በቦታው የተገኘችው የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ አስተያየታቸውን አሰባስባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ