1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤች አይቪ ሥርጭት በደቡብ ኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2011

ኢትዮጲያ የበሽታው ተህዋስ መጠን ተመልሶ በማንሰራራት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ መድረሱ ከተነገረ ወዲህ ጉዳዩ ዳግም ብሄራዊ አጀንዳ እየሆነ ይገኛል፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የተህዋሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ከሚታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ነው፡፡

https://p.dw.com/p/3917X
Weltaidstag 2011 Aids Seoul Südkorea
ምስል AP

ኢትዮጵያ፤ የኤች አይቪ ኤድስ ሥርጭት መከላከያዉ

በኢትዮጲያ ከጥቂት ዓመታት በፊት የኤ ች አይ ቪ ኤድስን ን ስርጭት ለመከላከል በተደረጉ ጥረቶች ቫይረሱ የሚገድለዉን ሰዉ ቁጥር በ70 በመቶ ለመቀነስ ተችሎ እንደነበር ይነገራል።ይሁን እንጂ መንግሥትም ሆነ ህብረተሰቡ ለበሽታው ይሰጡት የነበረው ትኩረት በመቀነሱ የበሽታው ስርጭት ከፍ እያለ መሔዱን የፌደራሉ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት አስታዉቋል። የኤች አይቪ ኤድስ ሥርጭት ከፍተኛ መሆኑ ከሚገመትባቸዉ አካባቢዎች፣ የደቡብ ብሄር እና ብሔረሰቦች ክልል አንዱ ነው።  የኤድስ በሽታ አማጭ ተህዋስ በኢትዮጲያ መኖሩ የታወቀው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በ1978 ዓም ነው፡፡ ከዛ በኋላ ባሉት ሁለት አሥርተ ዓመታት የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል ፤ ህጻናትን ያለወላጅ አስቀርቷል፡፡ በሽታው በዜጎች ማህበራዊ ሕይወት ላይ ጥቁር ጠባሳን ጥሎ ማለፉም የቅርብ ጊዜ አውነታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በኢትዮጲያ የበሽታው ተህዋስ መጠን ተመልሶ በማንሰራራት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ መድረሱ ከተነገረ ወዲህ ጉዳዩ ዳግም ብሄራዊ አጀንዳ እየሆነ ይገኛል፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የተህዋሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ከሚታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ነው፡፡ ሳኢትዮጲያ እንደአውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የኤች.አይ.ቪ አድስ ተህዋስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችላትን ብሄራዊ ዕቅድ ነድፋ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በበሽታው መጠነ ሥርጭት ላይ ከተካሄዱ የጥናት ውጤቶች እንጻር ሲታይ ግን አገራዊ ዕቅዱን ገቢራው ሥለማድረጓ ሲበዛ ያጠራጥራል፡፡ የፌደራል ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ፤ በኢትዮጲያ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ሴቶች መካከል 76 በመቶ ያህሉ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል እውቀት የላቸውም። በወጣቶች ዘንድ የሚስተዋለው የግንዛቤ ማነስ ታዲያ ፤ የበሽታው አማጭ የሆነው ተህዋስ የስርጭት መጠኑን እንዲያሰፋ ምክንያት እየሆነ እንደሚገኝ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡ በአገሪቱ በንግድና በቱሪዝም ዘርፎች ምክንያት ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር የሚካሄድበት የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ፤ የበሽታው ስርጭት ከሚታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቨ አድስ መከላከል ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳዊት መንግሥቱ ፤ በክልሉ ከሥኳር ፋብሪካዎችና ከእንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የበሽታው ተጋላጭነት እየሰፋ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡ በአሁኑወቅት በክልሉ የሚገኘውን የኤች አይ ቪ ኤድስ ተህዋስ የስርጭት መጠን መጠናቱን የገለጹት የፕሮግራሙ አስተባባሪ የበሽታውን ሥርጭት በመከላከል ረገድ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ሥራን ውጤታማ ለማድረግ ከመንግሥት የጤና ተቋማት በተጨማሪ  የባድርሻ አካላት ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከአነኝህ ባለድርሻ አካላት መካከል በኢትዮጲያውያን አቆጣጠር በ1999 ዓ.ም የተቋቋመው የደቡብ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ማህበራት ጥምረት በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ጥምረቱ በደቡብ ክልል ደረጃ በ25 ማህበራት የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአባል ማህበራት ቁጥር 92 መድረሱን የጥምረቱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ታደለች ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑወቅት በሽታውን በመከላከል ረገድ ቀደምሲል ይገኝ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ ቢቀንስም ፤ ጥምረቱ ግን በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ ሰብሳቢዋ ወይዘሮ ታደለች ይናገራሉ፡፡ የደቡብ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ማህበራት ጥምረት ሥር ከሚንቀሳቀሱት ማህበራት መካከል በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው ፋሪስ የተባለው ብሄራዊ ማህበር አንዱ ነው፡፡ ከኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር በሚኖሩ በጎ ፍቃደኞች የተቋቋመው የዚሁ ማህበር  ሥራአስኪያጅ  ወይዘሮ አስቴር ያቆብ ፤ አባሎቻቸውን ከመደገፍ አንጻር በመከናወን ላይ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ተከታዩን ብለዋል፡፡ በእርግጥ የኤች አይ ቪ ኤድስ የመከላከል ሥራ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚጠይቅ ይታመናል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን በክልሉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት አርስ በእርስ ተደጋግፎ በመስራት ረገድ ሰፊ ክፍተቶች እንደሚታዩባቸው የማህበራቱ አባላት ይጠቅሳሉ፡፡ የፋሪስ ብሄራዊ ማህበር መሥራች አባል የሆኑት አቶ ዳንኤል ተስፋዬ በበኩላቸው የኤች አይ ቪ ኤድስ ሥርጭትን በመከላከሉ ሥራ በመንግሥት በኩል የጎላ ቸልተኝነት እንደሚስተዋል ይናገራሉ ፡፡

Kinder im Aids Hospiz in Addis Abeba
ምስል AP Photo
Afrika Kinder Tabletten Medizin Gesundheit HELL
ምስል Getty Images/Marco Di Lauro

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ኂሩት መለሰ