1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"የእያሰሩ መፍታት አዙሪት መቆም አለበት"

ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2011

ሰሞኑን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲስ አበባ ያሰራቸውን ወጣቶች እንዲፈታ የሚጠይቅ ዘመቻ ሲያካሒዱ ከርመዋል። ወጣቶቹ የታሰሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮችን ለመቀበል በከተማዋ ተዘጋጅቶ በነበረ መርሐ-ግብር ወቅት ኹከት እና ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነበር።

https://p.dw.com/p/36eHi
Addis Abeba
ምስል Haile

የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲፈቱ የሚጠይቀው ዘመቻ

ሰሞኑን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲስ አበባ ያሰራቸውን ወጣቶች እንዲፈታ የሚጠይቅ ዘመቻ ሲያካሒዱ ከርመዋል። ወጣቶቹ የታሰሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮችን ለመቀበል በከተማዋ ተዘጋጅቶ በነበረ መርሐ-ግብር ወቅት ኹከት እና ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነበር። በከተማዋ ስለተፈጠረው ግጭት ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደግፌ በዲ የሰንደቅ አላማ አሰቃቀል ጉዳይ የግጭት መንስኤ መሆኑን ተናግረው ነበር። ጄኔራል ደግፌ ከሶስት ሳምንታት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኹከቱ ተሳትፈዋል ያሏቸው 1204 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረው ገልጸዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዜጎች "ለሕንጸት" ወደ ጦላይ መላካቸውንም ጄኔራል ደግፌ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። የታሰሩት ወጣቶች ለፍርድ አለመቅረባቸው እና ለረዥም ጊዜ ታስረው መቆየታቸው ያሳሰባቸው የማኅበራዊ ድረ-ገፆች ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ታዲያ ፍቷቸው ሲሉ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።  ዘመቻው ትንናት ተጀምሮ ነገ ይጠናቀቃል። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ