1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮምያና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰላም ጉባዔ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011

ቤኒሻንጉልን ከኦሮሚያ ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ካለፈዉ ክረምት ጀምሮ በተደረጉ ግጭቶች በመቶ የሚቆጠር ሰዉ ተገድሏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተፈናቅሏል። ግጭቱ እንዳይደገም ይረዳሉ የተባሉ ጉባዔና ዉይይቶች በተደጋጋሚ እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/3GWbo
Äthiopien Treffen der Regionalregierungen von Benishangul Gumuz und Oromia
ምስል DW/N. Dessalegn

በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በምዕራብ ኦሮምያ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ለበርካቶች መፈናቀል ምክንያት የሆነዉን ችግር ለመቅረፍ በአሶሳ ከተማ የሁለቱ ክልል ፕሬዚደንቶች ምኒስትሮች ሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት የማጠቃለያ የሰላም ጉባኤ ተካሂዶአል። በጉባዔዉ ላይ የኦሮምያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚደንት አቶ አሻድሉ ሃሰን እንዲሁም የሠላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ንግግር አድርገዋል። ቤኒሻንጉልን ከኦሮሚያ ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ካለፈዉ ክረምት ጀምሮ በተደረጉ ግጭቶች በመቶ የሚቆጠር ሰዉ ተገድሏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተፈናቅሏል። ግጭቱ እንዳይደገም ይረዳሉ የተባሉ ጉባዔና ዉይይቶች በተደጋጋሚ እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል። በጉባዔዉ ላይ የተገኘዉ የአሶሳዉ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

Äthiopien Treffen der Regionalregierungen von Benishangul Gumuz und Oromia
ምስል DW/N. Dessalegn


ነጋሳ ደሳለኝ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ       

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ