1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከተማ ወንዞች ልማት ፕሮጀክት

ዓርብ፣ የካቲት 15 2011

ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሏል። ይህ የወንዞች ልማት ፕሮጀክት የታሰበው አዲስ አበባን አቋርጠው በሚያልፉ በኹለት ታላላቅ ወንዞች አጠቃላይ 27,5 ኪሎ ሜትር ርዝመትን አካልሎ ሊሠራ ነው።

https://p.dw.com/p/3Dtd4
Äthiopien Stadtverwaltung von Addis Abeba
ምስል DW/Yohannes G/Egziabhre

 
2,5 ቢሊየን ብር ይፈጃል የተባለው የአዲስ አበባ ወንዞች የመናፈሻ ልማት ሥራ ፕሮጀክት ትናንት ይፋ ሆኗል። ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሏል። ይህ የወንዞች ልማት ፕሮጀክት የታሰበው አዲስ አበባን አቋርጠው በሚያልፉ በኹለት ታላላቅ ወንዞች አጠቃላይ 27,5 ኪሎ ሜትር ርዝመትን አካልሎ ሊሠራ ነው። ከከተማዋ ልማት አኳያ ፈጣን ለውጥን የማምጣት ኃይል እንዳለው የተገለፀው ፕሮጀክት ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ የሚዘረጉት ወንዞች ላይ እንደሚተገበር ተገልጿል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ