1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣት ኢትዮጵያውያን የስደት መንስኤ እና መፍትሄው

ዓርብ፣ ሚያዝያ 23 2007

የወጣት ኢትዮጵያውያን የስደት መንስኤ እንደ የግለሰቡ ይለያያል፤ ቢሆንም የበርካቶች ተመሳሳይ ነው። ስራ አጥነት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ዋንኞቹ እንደሆኑ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልፀውልናል።

https://p.dw.com/p/1FIOd
Bildergalerie Rettung von Flüchtlingen durch deutsche Cargo schiffe im Mittelmeer
ምስል OOC Opielok Offshore Carriers

ለወጣት ኢትዮጵያውያን የስደት መንስኤ ስለሆኑ ምክንያቶች እና የወጣቶቹ የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ዝግጅቱ ያተኩራል። ወጣት መሐመድ ከስራ አጥነት ባሻገር ወጣቱ ሀገር ለቆ የሚሰደድበትን ምክንያት ሲገልፅ፤ ነፃነት እና የገቢ አለመጣጠንን በምክንያትነት ያስረዳል። ዮሀንስ የሚባለው ሌላው ወጣት ደግሞ ከሰማሁት እና ካየሁት፤ በርካታ ወጣቶች ሀገራቸውን ትተው የሚሰደዱበት ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ሲሆን መፍትሄው የፖለቲካ አሠራሩ እንዲሻሻል ይጠቁማል።የዮንቨርስቲ ተማሪ የሆነው ወጣት ፋብሩ አመለካከት ደግሞ ትንሽ ለየት ይላል፤« ስራ አጥነት ሰራተኛው የፈጠረው ነው«» ይላል።

ፋብሩ፤ ኢትዮጵያውያን የሚሰደዱት በአቋራጭ ለማደግ ነው ሲል፤ በአሁኑ ሰዓት ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በስደት ላይ የሚገኘው አዲስ፤ ምክንያቱን በአጭሩ ሲገልፀው፤ «መንፈሳዊ ቅናት» ነው። ሳሙኤል የተባለውም ወጣት ርዕርስ በዕርስ የመተያየት ችግር አለ ይላል።ኤልያስ የተባለው ወጣት ደግሞ ለወጣት ኢትዮጵያውያን የስደት መንስኤ ናቸው ሲል፤ ከስራ አጥነት እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በተጨማሪ ፤ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ እንዳለ ገልፆልናል። የሁሉንም አስተያየት በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ