1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ የጦር ቅነሳ እቅድ እና አፍሪቃ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 22 2011

ወታደራዊ ትኩረቷን እንዳዲስ በቻይና እና በሩስያ ያሳረፈችው  ዩኤስ አሜሪካ በአፍሪቃ ያሏትን የጦር ኃይል ቁጥር ለመቀነስ እንዳቀደች ተሰምቷል። ይህ እቅድ በፀጥታ ጥበቃ ጠበብት ዘንድ የተጠበቀ ነበር፣ ጠበብቱ ወደፊትም ሌሎች ቅነሳ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

https://p.dw.com/p/39EKT
Afrika Senegal US Soldaten
ምስል Getty Images/AFP/Seyllou

የዩኤስ የጦር ቅነሳ እቅድ እና አፍሪቃ

ዩኤስ አሜሪካ ከአፍሪቃ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ የመቀጠል ኃላፊነቷን ልትወጣ  እንደሚገባ ከፍተኛው አንድ ከፍተኛ የዩኤስ አሜሪካ ጦር  መኮንን ተማፀኑ። ይህን ተማፅኖ ለሀገራቸው ምክር ቤት ባለፈው በጎርጎሪዮሳዊው መጋቢት፣ 2018 ዓም  ያሰሙት ጀነራል ቶማስ ዎልድሀውዘር በአፍሪቃ የዩኤስ አሜሪካ ጥቅም ለረጅም ጊዜ  በተሻለ መንገድ ሊጠበቅ የሚችለው ዩኤስ በአፍሪቃ ስትቆይ መሆኑን አስረድተዋል። ዎልድሀውዘር አክለው እንዳመለከቱት፣ በአፍሪቃ የተረጋጉ /// ፍቱን ተጠያቂ የሆኑ መንግሥታት፣ እንዲሁም፣ በሚገባ የሰለጠኑ ስርዓት የጠበቁ ጦር ኃይላት እና ኤኮኖሚያዊ እድገት የሚያሳዩ ሀገራት የሚኖሩበት ሁኔታም የበለጠ ጠቃሚ ሊሆን ነው። ይሁን እንጂ፣ የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት፣ ቢያንስ በከፊል ወደ ሌላ አቅጣጫ በመሄድ ላይ ያለ ነው የሚመስለው። የዩኤስ አሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር ፣ ፔንታገን  በአፍሪቃ ያሰማራውን ጦር በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ለመቀነስ ማቀዱን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉን የፔንታገን ቃል አቀባይ ካንዲስ ተሬሽ አስታውቀዋል። ዩኤስ አሜሪካ በወቅቱ በአፍሪቃ  7,200 ወታደሮች  እና ሲቭል ሰራተኞች አሏት። 
« የብሔራዊ መከላከያ ስልት በ2017 ዓም ነበር እንደገና የተጻፈው። በዚሁ ስልት ከሰፈሩት ሀሳቦች አንዱ ዩኤስ አሜሪካ ወታደራዊ ትኩረቷን ትልቅ ስጋት  ደቅነዋል ባለቻቸው ቻይና፣ ሩስያ እና እነሱን በመሰሉ ሀገራት ላይ ማዞሯን ያሳያል። በዚሁ መሰረትም፣ የመከላከያ ሚንስትሩ በዩኤስ ጦር ኃይላት ውስጥ ያሉትን ፀረ አክራሪ ድርጅት ታጋይ ቡድኖች ሁኔታ እንዲጠና ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። »
ባለፈው ጥር ወር የወጣ አዲሱ ሰነድ በተለይ ትኩረቱን ያሳረፈው አሁን እንደገና ከቻይና እና ከሩስያ ጋር ለተጀመረው ስልታዊ ፉክክር ነው። ከፅንፈኛ ቡድኖች የተደቀነው ስጋት የዩኤስ አሜሪካ ጦር በአፍሪቃ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ ዋነኛ ትርጉም እንደያዘ ቢገኝም፣ ቅድሚያ የሰጠው ጉዳይ ግን አለመሆኑ ታውቋል። በአዲሱ የዩኤስ ስልት መሰረት፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የዩኤስ ጦር እዞች በየአካባቢዎቹ በተሰማሩት የሀገራቸው ጦር ኃይላት ቁጥር ላይ ቅነሳ ሊደረግ የሚቻልበትን ጉዳይ እንደሚፈትሹ ይጠበቃል። 
የፔንታገን ባለስልጣናት በአፍሪቃ የሚደረገው የጦር መሳሪያ ቅነሳ ሊያስከትል የሚችለውን መዘዝ በተቻለ መጠን አስተናንሰው ለማቅረብ እየሞከሩ ነው። ቅነሳው የሚደረግባቸውን ቦታዎች ከመግለጽም የተቆጠቡት የፔንታገን ቃል አቀባይ ካንዲስ ትሬሽ፣ ሀገራቸው የአክራሪ ፅንፈኛ ድርጅቶችን ተግባር ለማክሸፍ እና ጥቃት የመጣል አቅም እንዳይኖራቸው ማድረጓን እንደማታቋርጥ ገልጸዋል።  ዩኤስ አሜሪካ በጅቡቲ የጦር ሰፈር ቢኖራትም፣ የጦር ኃይሎችዋ ሶማልያን፣ ናይጀሪያን እና ኒጀርን በመሳሰሉ ሌሎች ሀገራትም እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት ትሬሽ፣ ሀገራቸው የጦር ኃይል አባላቷን ከመቀነሱ ጎን ሌላ አሰራር መከተል መጀመሯን አመልክተዋል።
«  በሌሎች ምዕራብ አፍሪቃን በመሳሰሉ ቦታዎች ከታክቲካዊ የአማካሪነት ስራ አሁን  የስለላ መረጃ ወደምንለዋወጥበት፣ ስልጠና ወደምንሰጥበት መሰል ተግባራት እየቀየርን ነው፣ ይህም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል።  ቅነሳው በየትኞቹ ሀገራት እንደሚደረግ ልነግርህ አልችልም። ይሁንና፣ ቻድን በመሳሰሉ ሀገራት ውስጥ የአክራሪ ድርጅቶችን ተግባር ለማጨናገፍ እና ለማክሸፍ መስራታችንን እንቀጥላለን። ፅንፈኛ ድርጅቶቹ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበት አንድም ክፍት ቦታ  አንተውላቸውም፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የትኩረታችንን አቅጣጫ መቀየር ብቻ ነው። »

Militärmanöver Flintlock im Niger
ምስል DW/A. M. Amadou
Infografik US Armee in Afrika EN

የዩኤስ አሜሪካ ዕለታዊ ጋዜጣ ኒው ዮርክ ታይምስ ባለፈው መስከረም ወር ያወጣው አንድ ዘገባ፣ ሀገሩ በአፍሪቃ የሚገኙ ፀረ ሽብርተንነት ጦር ቡድኖችን በጠቅላላ ለማስወጣት በማሰላሰል ላይ መሆኗን አስታውቆ ነበር። ጀነራል ቶማስ ዎልሀውዘርም ለሀገራቸው ምክር ቤት ባሰሙት  ባቀረቡት መግለጫቸው ላይ በአፍሪቃ ዋናው የዩኤስ ጦር ሚና  ስልጠና እና ርዳታ መስጠት መሆኑን ነበር ያስታወቁት።  ይህ የዩኤስ አሜሪካ ጦር በውዝግቦች ውስጥ ራሱ የዋነኛ ተንቀሳቃሽነት ሳይሆን የድጋፍ ሰጪነት ሚና መያዝ መጀመሩን፣ ማለትም፣ የፀጥታ ጥበቃ ተግባራት የአጋር ሀገራት የፀጥታ ኃይላት ራሳቸው ሊወጡ እንደሚገባ የሚያጎላ መሆኑን ጀነራሉ ገልጸዋል።   
የዩኤስ አሜሪካ ጦር ኃይላት በአፍሪቃ ጥቃት ደርሶባቸዋል፣ በ2017 ዓም በኒጀር በተጣለ የደፈጣ ጥቃት አራት አሜሪካውያን ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል። ጥቃቱ የዩኤስ አሜሪካ ጦር በአፍሪቃ የሚያካሂደውን የጦር እንቅስቃሴ ይፋ ባወጣበት ጊዜ ከኒጀር ህዝብ ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል። ይህን ተቃውሞ ተከትሎም አሜሪካ  ትቅደም የሚል ፖሊሲ የያዘው  የዩኤስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር  በአፍሪቃ ያለውን ጦሩን  ስጋት ደ,ቅነዋል ወደሚላቸው ሌሎች አካባቢዎች የማዘወር እቅድ ይዞ መውጣቱ ለፀጥታ ተንታኞች አስገራሚ እንዳልነበረ ዳካር፣ ሴኔጋል የሚገነው የፀጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ ተንታኝ ፎንቴ አኩም ለ DW ተናግረዋል።
« አሜሪካውያን የመከላከያ ባለስልጣናትን ሲናገሩ ብትሰማ፣ በዩኤስ አሜሪካ ጦር ተግባር ላይ፣ ማለትም፣ በአፍሪቃ በሚያካሂደው የስልጠና፣ የምክር እና ርዳታ የማድረግ ተልዕኮ ያስገኘው ውጤት የተለያየ መሆኑን ትገነዘባለህ። አንዳንዶች ካሜሩንን ከመሰለ ሀገር ጋር ያላቸው ግንኙነት ከስራ ውጭ እንዳደረጋቸው ሲናገሩ ይሰማሉ። በሌላ በኩል ግን፣ ከሌሎች ሀገራት ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ የሀገራቱን ጦር በጦር ሜዳ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ እንዲችሉ አድርገው ማሰልጠን እንዳልተሳካላቸው  ይሰማሉ። በሶማልያ የሚጫወቱትን ሚና ሳይቀር እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ። በአሸባብ አንጻር ጅቡቲ ከሚገኘው የጦር ሰፈራቸው ጥቃት ቢያካሂዱም፣ አሸባብ አሁንም መንቀሳቀሱን አላቋረጠም። »
እንደ የፀጥታ ጥበቃ ጉዳዮች ተንታኝ ፎንቴ አኩም አስተሳሰብ፣ አሁን የታሰበው የጦር ኃይላት ቅነሳው ምን ሊያስከትል እንደሚችል አሁን መናገር አይቻልም፣ ይሁንና፣ ቅነሳው በዚሁ እንደማቆም አስጠንቅቀዋል። 
«  ከ720 ው  10 ከመቶውን ብትወስድ እና  በሩስያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ወይም ሰሜን ኮርያ ብታሰማራ፣ ይህ ዩኤስ አሜሪካ ከነዚህ ሀገራት ሊደቀንባት ከሚችለው ስጋት ሊከላከላት ይችላል በቂ ነው ወይ ብለህ ራስህን መጠየቅ ይኖርብሀል። እርግጠኛ አይደለሁም። ስለዚህ ከጠየቅኸኝ ወደፊት ለሌሎች ብዙ ቅነሳዎች ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን። » 

Dschibuti Übung des US-Militärs
ምስል picture-alliance/dpa/US Air Force/N. Byers
USA Ankunft der toten US-Soldaten aus dem Niger
ምስል picture alliance/AP Photo/L. Hiser/U.S. Army

አርያም ተክሌ/ዳንየል ፔልስ

እሸቴ በቀለ