1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድምፅ ቆጠራ ሂደት በዚምባብዌ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2010

የዚምባብዌ ዜጎች ሀገራቸውን ከምትገኝበት የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር ያወጣል ብለው ተስፋ የጣሉበትን  የመጀመሪያ የምርጫ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።  ትናንት በሀገሪቱ የተካሄደው የመጀመሪያው ድህረ ሙጋቤ አጠቃላይ ምርጫ ድምፅ ቆጠራ አንዳንድ የመጀመሪያ ውጤቶች በመዲናይቱ ሀራሬ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ተለጥፈዋል።

https://p.dw.com/p/32OFx
Simbabwe Wahl Auszählung
ምስል Gettey Images/AFP/M. Longari

የመጀመሪያው ድህረ ሮበርት ሙጋቤ ምርጫ

ዓለም አቀፍ ቡድኖች በቅርብ በመከታተል ላይ ያሉትን የድምፅ  ቆጠራ ሂደት የመጨረሻው ውጤት ከጥቂት  ቀናት በኋላ እንደሚያወጣ አስመራጩ ኮሚሽን አስታውቋል።
በቅርቡ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው የትናንቱ የዚምባብዌ አጠቃላይ ምርጫ ውጤት እስከ ቅርብ ጊዜ በፊት ተገልላ የነበረችውን ሀገር ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ በመመለስ ኤኮኖሚያዊ ተሀድሶ እንደሚያስገኝ የዚምባብዌ ዜጎች  ተስፋ አድርገዋል።  የዚምባብዌ አስመራጭ ኮሚሽን በሰላማዊ መንገድ  ተካሂዷል ያለውን ምርጫ የመጀመሪያ ውጤት ዛሬ እንደሚያወጣ የሚጠበቅ ሲሆን በዚምባብዌ አስመራጭ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ዳና ፕሪሲሊያ ቺጉምባ መግለጫ መሰረት፣ ለምርጫ የወጣው የህዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር። 
« እስካሁን በደረሰን እና በማጣራት ላይ ባለነው መዘርዝር መሰረት፣ ባንዳንድ አካባቢዎች የመራጭ ተሳትፎ ከ60 እስከ 78 ከመቶ  ነው። ኮሚሽኑ በገጠመ የመጓጓዣ ችግር የተነሳ እስካሁን ከጥቂት ራቅ ብለው ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ብቻ ነው ውጤት ያልደረሰው።  በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ግን  የድምፅ ቆጠራው ተጠናቋል። »
የዚምባብዌ ዜጎች ሀገራቸውን ከምትገኝበት የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር ያወጣል ብለው ተስፋ የጣሉበትን  የመጀመሪያ የምርጫ ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደመሆናቸው መጠን፣ ኮሚሽኑ ለዚሁ የሕዝቡ ትፅቢት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ቢሰጥ መልካም እንደሚሆን አንዱ መራጭ ገልጸዋል።
«  ጥሩ የሚሆነው ፣ ሁሉ ሰው እንዲረጋጋ ውጤቱን  በተቻለ መጠን ቶሎ ቢያወጡ ይመስለኛል።እንደሚመስለኝ፣ነው። ምክንያቱም ሰዎች ገና አልተረጋጉም። ብዙ ነገር ይሆናል ብለው በማሰብ ላይ ናቸው። ጥሩ የሚባል ለውጥ ያስፈፈልጋቸዋል። ይህን ነው የሚጠብቁት። »
ቆጠራው በቀጠለበት ባሁኑ ጊዜ ሀቀኛ የሀራሬ ነዋሪ ታዋንዳ ኂርሙታን የመሳሰሉ ዜጎች ምርጫው ለውጥ እንደሚያስገኝ እምነታቸውን እየገለጹ ነው።
« ሀቀኛውን  ለውጥ አሁን እያየሁ ነው። የመንግሥት ለውጥ እንደሚኖር፣ ስልጣኑ ከዛኑ ፒ ኤፍ ወደ ኤም ዲ ሲ እንደሚቀየር አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ጠቋሚ መሆኑን እያየሁ ነው። »
ሻድሬክ ዱቤ ም ለውጥ የማየት ጽኑ ፍላጎት ነው ያላቸው። 

Simbabwe Präsidentenwahl
ምስል Reuters/M. Hutchings

«   በዚምባብዌ ለውጥ እንዲመጣ እንፈልጋለን። ድምፄን ስሰጥ ምንም ዓይነት ማበርበር አልታዘብኩም።  »
በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ከተወዳደሩት 23 እጩዎች መካከል የወቅቱ ር/ብ የ75 ዓመቱ የቀድሞውን ፕሬዚደንት የተኩት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና የተቃዋሚው ህብረት እና የዴሞክራሲያዊ ለውጥ ንቅናቄ፣ በምህጻሩ ኤምዲሲ መሪ እና  እጩ ጠበቃ ኔልሰን ቻሚሳ ወደ ድል እያመሩ መሆኑን ነው የገለጹት።  ምናንጋግዋ ፓርቲያቸው ዛኑ ፒኤፍ በድምፅ ቆጠራው  በጣም አዎንታዊ ውጤት እያሳየ ነው ሲሉ፣  ኔልሰን ቻሚሳም በበኩላቸው ፓርቲያቸው ደርሰውታል ባሏቸው ከ10,000 የሚበልጡ ጣቢያዎች ውጤቶች መሰረት፣ በጣም እየቀናው ነው ብለዋል። ይሁንና፣ ባንዳንድ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራው ውጤትን ሆን ብሎ አላወጣም ሲል የተቃዋሚው ቡድን ቅሬታውን እያሰማ ነው።  
የፕሬዚደንታዊው፣ ምክር ቤታዊ እና ያካባቢ ምክር ቤቶች ምርጫ ውጤቲት እስከፊታችን ቅዳሜ ስለሚጠበቅ አሸናፊው ለሚቀጥሉት በርካታ  ቀናት አይታወቅም። 
የኮሚሽኑ ኃላፊ የመራጩ ድምፅ እንደሚከበር  አረጋግጠው፣ የኮሚሽኑ ኃላፊ የመራጩ ድምፅ እንደሚከበር አረጋግጠው፣ አንዱም እጩ 51  ከመቶ የመራጭ ድምፅ ካላገኘ ነሀሴ ስምንት የመለያ ምርጫ ይደረጋል።  

Bildkombo Simbabwe Präsidentschaftswahlen Mnangagwa Chamisa
ምስል picture-alliance/AP Photo

    
አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ